Page 1 of 1

56ቱ የደቡብ ብሄሮች 56 ክልሎች ይሁኑ ወይስ አይሁኑ? ለምን?

Posted: 03 Jan 2020, 01:09
by Horus
በዚህ ሰሞን ብዙ የሚያስገርሙ አስተያየቶች እሰማለሁ ።

እኔ በመሰረቱ ኢትዮጵያን በ85 ክልሎች መከፋፈሏን ህይወቴን ሙሉ የተቃወምኩት ነገር ነው።

ከልል የጦርነት ምንጭ፣ የድህነት ምንጭ ነው። ወደ ፊትም ክልል ማንም ፋይዳ አይፈይድም ።

ስለሆነም ኦሮሞ። አማራ፣ ሌላው ሌላው ክልል እንዲፈርስ የሚሰሩ ከሆነ አሁን ክልል የሌላቸው 75 ብሄሮች የክልልነት ንቅናቄያቸው እንዲያቆሙ እንተቻለን ።

ነገር ግን አዳሜ የራሷን ክልል እያጦፈች ሌሎችን አትከልሉ ማለት አጉል ብልጥነት ወይም ትምክህት ይመስለኛል ።

መደረግ ያለበት ሌሎች እንዳከለሉ መብታቸውን መርገጥ ሳይሆን የክልል ፍልስፍና ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ ማድረግ ነው ።

አዜማም፣ ብልጽግናም፣ ሌሎቹም ጥርስ አልባ የወሬ ሱቆች ይህን ማድረግ ግድ ይላቸዋል ።

በዚህ ዘመን ማንም ብሄር የማንም ሌላ ብሄር ጥገኛ አይሆንም ። ቁልፉ የብሄር ፖለቲካን ማክሰም ነው !!