ሰበር ዜና፣ የ ፍየልና በግ መዋጮ ግዳጅ ለየካቲት 11 በዓል!
Posted: 02 Jan 2020, 14:11
ህወሃት ከመንግስት ሰራተኞች ለየካቲት 11 በአል በማለት ከወር ዶሞዛቸው መቁረጥዋ ሲገርመን አሁን ደግሞ በየገጠሩ እየዞረች ከዚህ ድኃ ገበሬ ላይ። ፍየልና በግ አዋጡ እያለች በካድሬዎች አመካኝነት እያሰባሰቡ እንደሚገኙ እራስዋ በድምፂ ወያኔ ቴሌቪዥን ያለ እፍረት እየተናገረች ነው። የዘንድሮው በአልዋ ልዩ የሚያደርገው የፌደራል ኃይሎች ብላ እነ አየለ ጫሚሶና ትእግስቱ አዎሉ ሌሎች ሆዳሞች ጭምር ይህንን የቁም ተዝካር አብረው እንደሚያከብሩት ነው።

