Page 1 of 1

ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ

Posted: 01 Jan 2020, 18:45
by simbe11
ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ ብሎ ሰበር ዜና::
ድብደባና የግለሰቦች የገቡበት መጥፋት ዛሬ የተጀመረ ይመስል::
ህወሃት ላለፉት አርባ ምናምን አመታት ስትገድልና ስትዘትፍ እንደኖረች እየታወቅ ይህን ሰበር ዜና ብሎ ማቅረብ አይነፋም!!!


https://mereja.com/amharic/v2/192816

Re: ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ

Posted: 01 Jan 2020, 18:50
by tarik
ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ
January 1, 2020 – ውብሸት ታዬ — Comments ↓
Facebook
Twitter
Email
Share

በሕወሃት ተጠርቶ የነበረውና ‹‹የትግራይ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ›› የተሰነው ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ በክልሉ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ከህግ አግባብ ውጪ የእስር እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የአረና ትግራይ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ በተለይ ለመረጃ ቲቪ ገለጹ፡፡
እንደ አቶ አብርሃ አገላለጽ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የሕወሃት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል ምክትል መስተዳድር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ‹ድርጅታችንን በሚቃወሙ ሁሉ ላይ እርምጃ እንወሰወዳለን› ሲሉ ባወጁት መሰረት ድብደባና እስሩ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

እስካሁን 21 የትግራይ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ አቶ ሃደራ ወሉ እና አቶ መሀሪ ተክሌ በተባሉ ሁለት የአረና አባላት ላይ ድብደባ ከተፈጸመ በኋላ ለእስር እንደተዳረጉ ተገልጧል፡፡ ህወሃትን የሚቃወም በሙሉ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ጫና እየተደረገ መሆኑንም ሊቀ መንበሩ ተናግረዋል፡፡
አቶ አብርሃ የትግራይ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት በፍርሃት ተሸብቦ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመበት እንደሆነ አስታውስው ከቀጣዩ ምርጫ ጋር በተያያዘ ፓርቲያቸው ዝግጅት እያደረገ ቢሆንም በተጨባጭ በትግራይ ምርጫ መደረጉ አጠራጣሪ እንደሆነባቸው ለመረጃ ቲቪ ገልጸዋል፡፡

Re: ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ

Posted: 01 Jan 2020, 18:53
by Digital Weyane
Tigray is the land of internationally recognized Human Rights activists like my Weyane brother Awash and myself. So how can there be human rights violations in a country that has championed human rights? It doesn't make any sense. We even respect the human rights of our domestic and wild animals in Tigray, let alone humans! :evil: :evil:

Re: ሰበር ዜና: በትግራይ ድብደባና እስር ተጀመረ

Posted: 01 Jan 2020, 19:57
by simbe11
እኔን የገረመኝ ሰበር ዜና ምባሉ ነው:: ለ27 አመታት ሰውን ሲሰባብሩት ኖረው እንደ አዲስ::
ህወሃት የተለመደውን ድብደባ አጥብቆ እየገፋበት ነው ቢባል ያስኬዳል::