ሆረስ እባላለሁ፣ ቃል መሰንጠቅ አይመቸኝም ፣ ባንድ ቃል ይህው !
ማየት እስከሚያቅት ድረስ ብዙ ኦሮሞ ወጣቶች የወታደር ልብስ ለብሰው በረድፍ ተስልፈዋል ። እሺ ለምን?
ለወጣት ስራ ፈጠራ ።
አሁን ካሉት የኦሮሞ ፖሊሶች እና ወታደሮች ደምሩ ።
በኦሮሞ ያለው የስራ መስክ ውትድርና ብቻ የሆነ ይመስለኛል ። ይህ ደሞ ለኦሮሞ የረጅም ጊዜ ችግርና ቀውስ ነው ። ለምን?
አንደኛ፣ ወታደር አምራች ሃይል አይደለም ። ባሁን ዘመን በዘረፋ ወይ በወረራ መብላት ስለማይቻል ወታደር ሳይሰራ የሚቀለብ ህዝብ ነው። አርቀው ለማያስቡ የወታደር እና የፖሊስ ብዛት ህይል የሚሰጣቸው ይመስላቸዋል። ግዙፍ ስህተት !!
ይህ እጅግ መጥፎ ጎጂ ካልቸር ነው ።
ሁለትኛ ፣ ውትድርና የሚገባ ወጣት ሁሉ የማያድግ፣ የማይማር፣ የማይከብር፣ የማይሻሻል በመንግስት ተቀላቢ፣ የመንግስት ጥገኛ ኢንዱስትሪ ነው።
ኦሮሞ 60 ሺ የወጣት ወታደር ህዝብ ከመፍጠር 60 ሺ ወጣት የሚቀጥር አንድ ፋብሪካ ቢያቆሙ ብልህነት ነበር።
ሶስተኛ ፣ ወታደር ደሞ መጨረሻ ላይ የራሱን ህብረተሰብ ነው የሚበላ !
ሚሊተራይዘድ የሆኑ አገሮችን ታሪክ አስተውሉ ።
አራት፣ ወታደርና ፖሊስ የሚበዛበት (ሰርተው ማይበሉ) ቦታ በጉቦ፣ ሙስና፣ ሌብነት ፣ ወንጀል የሚበዛበት አገር ነው፣ ያ ነው ኦሮሞ የሚሆነው !!
ኬር