-
Hameddibewoyane
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42
በፌዴራል መንግስት ላይ ጦርነት ያውጀን ሃይል ለመደምሰስ!!!!
ትህነግ በፌዴራል መንግስት ላይ ጦርነት ካወጀች 3ተኛ ቀኑ ነው።ጠ/ሚ አብይ አህመድ፣ እንደ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ጦርነት ቢሸሽ ተገቢ ነው። ግን ደግሞ ጦርነት እንደ ክፉ ጥላ እየተከተለው ነው። ሆኖም ግን አብይ “ትህነግ ለጦር፣ እኛ ለፍቅር!” በማለት ቆርጦ የተነሳን የኢትዮጵያ ጠላት በጥሩ ቃላት ሸምግዬ እገላገላለሁ የማይልበት ደረጃ ደርሷል። ይህ ፈተና የኢትዮጵያ የመኖር እና አለመኖር ጉዳይ ነው። የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ፅንፈኛ መከታ የሆነችው ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ተመታ ድምጥማጥዋ እንድትጠፋና የምንወዳት ሀገር ህልውና እንዲቀጥል፣ አብይ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብን ያቀፈ ሀገራዊ ዝግጅት ለማድረግ ከአሁኗ ሰዓት መንቀሳቀስ አለበት።