Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 47506
Joined: 30 May 2010, 23:04

chika angol Amharu: ጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ

Post by Halafi Mengedi » 30 Dec 2019, 17:14

ጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ።
December 30, 2019 – Konjit Sitotaw — Comments ↓

ታህሳስ 9 ቀን ከጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ። ታዳጊዎቹ የተገደሉት አጋቾች በአንድ ሰው የጠየቁትን 100ሺህ ብር ወላጆች መክፈል ባለመቻላቸው ነው።

ከ8-15 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ታደጊዎች ከጠገዴ ወረዳ ዳውጨና ቀበሌ ወደ ታች አርማጭሆ ወረዳ ከተወሰዱ በኅላ በትናንትናው ዕለት ነበር በጥይት ተመተው የተገደሉት። ከሟቾቹ መካከል የ4ቱ አስከሬን አሰሳ በሚያደርጉ የመንግስት ሚኒሻዎች ተገኝቷል

ከቀናት በበፊት በምዕ/ጎንደር ዞን ከቋራ ወደ ሽንፋ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪን ውስጥ የነበሩ 6 ሰዎች በታጣቂዎች ከታገቱ ሰዎች መካከል፣ የመኪናው አሽከርካሪ ትናት ከሰዐት በኅላ ተለቋል። አሽከርካሪው የተለቀቀው ቤተሰቦቹ 300,000 ሺህ ብር ከከፈሉ በኅላ ነው።

ባለፉት 2 ዓመታት በምዕራብ ጎንደር ዞን በርከት ያሉ ሰዎች በታጣቂዎች የታገቱ ሲሆን፣ በተለይ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የችግሩ ዋና ሰለባ ሆነው ቆይተዋል። ታጣቂዎች አሽከርካሪዎችን ለመልቀቅ ከ200,000 እስከ 400,000 ብር ይጠይቃሉ።

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 47506
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: chika angol Amharu: ጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ

Post by Halafi Mengedi » 30 Dec 2019, 17:21

Addis Standard @addisstandard

#Ethiopia: Of 8 young kids who were kidnapped while tending cattle in #Tegede wereda, N.#Gonder zone, #Amhara region, 6 were reportedly killed by their kidnappers, as per 👇. Kidnappers demanded a ransom of 100, 000 br per child. 4 of the bodies were discovered by security forces
Ethiopia Live Updates @Ethiopialiveupd

ታህሳስ 9 ቀን ከጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ። ታዳጊዎቹ የተገደሉት አጋቾች በአንድ ሰው የጠየቁትን 100ሺህ ብር ወላጆች መክፈል ባለመቻላቸው ነው።

Post Reply