-
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42
በትግራይ ተቃዋሚ ሆኖ መንቀሳቀስ በናዚ ካምፕ ውስጥ ይሁዳዊ ሆኖ እንደመገኘት ያክል ነው!
የማያባራው ቅጣት አያድርስ ነው። አብዛኛው ወጣት ይህን የትህነግ ጭካኔ በመፍራት የትህነግ ወዶ-ገብ ደጋፊ፣ ተቃዋሚን ተናዳፊ ሆኖ ህሊናውን ሽጦ ይኖራል። ሌላውም ፌስ ቡክ ላይ ሰፍሮ ዞምቢ ሆኖ ይኖራል። በዚህ ክልል ያሉት እንደነ አብርሃ ደስታ፣ አምዶም ገ/ስላሴ፣ ነብዩ ስሑል ሚካኤል፣ ኃይለኪሮስ ታፈረ፣አሰፋ ትኩዕ፣ ሚኪ ተስፋይ፣የማነ ንጉስ ፣ህድሮም፣ፀጋይ ወዘተ እና በባለስልጣን ደረጃ ደግሞ ዶ/ር አብርሃም በላይ አይነት ወጣቶች የተላበሱት ወኔ በእውነት እነዚህ እንደኛው ሰዎች ናቸው ወይ የሚያሰኝ ነው። የነዚህ ወጣቶች እየተበራከቱ መሄድ፣ ትህነግን ረዘም ላለ ጊዜ ስንቃወም ለኖርነው ከፍተኛ የመንፈስ እርካታን ፈጥሮልናል።