Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም" ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ‼

Post by Ejersa » 28 Dec 2019, 21:14

ዶ/ር አብራሃም በላይ Awraamba Times ላይ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ኢንሳን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ መሆናቸውን በመጠቆም ወደ ኢንሳ የገቡት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ባስመዘገበው ውጤት እና መልካም ስነ-ምግባራቸው መሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር አብራሃም ለውጡን ተከትሎ የኢንሳ መስራች አመራሮች (ጓደኞቻቸው) በተለያየ የስልጣን ቦታ እና የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ገብተው መለያየታቸው እና ሁሉም እንደበፊቱ ለአገራዊ ዓላማ በአንድነት መስራት አለመቻላቸው እንደሚያሳዝናቸው በመጠቆም ከጓደኞቻቸው አንድም ሰው እንዲታሰር እና የሌላ አጀንዳ አራጋቢ ሆኖ ማየት እንደማይፈልጉ ለአገር ልማት ብቻ መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ዶ/ር አብረሃም በላይ ለትግራይ ጥቅም እንታገላለን በሚል ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ እና ተከታዮቹን ሃሳብ እንደሚቃወሙት በዚህም መሰረት ለአገር መስራቱን እንደቀጠለ በመግለፅ የጄ/ል ተክለብርሃንን ሃሳብ አሁንም እንደማይቀበሉት እነሱ ግን በስጋት ወደ መቀሌ መሸሻቸውን ጠቁሞ ማንም ሰው ወንጀለኛ ከሆነ ደግሞ ትግራይ ስለሄደ ከመታሰር አይቀርለትም! የትግራይ ህዝብ ለውጥ ፈላጊ እንጂ የለውጥ አደናቃፊ አይደልም የትግራይ ህዝብ አሁን ፌዴራል መንግስት ጫና እየፈጠረብን ነው ተብሎ ስጋት ውስጥ እንዲኖር ሆን ተብሎ የተለጠጠ ወሬ እየተነዛበት ነው እንጂ ምንም ስጋት የለም ብለዋል የትግራይ ህዝብም የለውጡ አካል ሆኖ ሳለ የመጣውን ለውጥ የእኔ አይደለም ብሎ መሸሸ ልክ አይደለም።

ዶ/ር አብይ አህመድ እኛ ትግሬዎች ለትግራይ ህዝብ ያላደረግነውን ሲያደርግ የነበረ አሁንም ኣብዛኞቹ ጓደኞቹ የትግራይ ልጆች ናቸው መጀመሪያ አከባቢ የንግግር ግድፈቶች ነበሩ እሱን ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ስለ ሌባ ሲናገር የትግራይ ህዝብን ሌባ ብሎ ሰድቧል በሚል እየለጠጡት ስለሆነ እንጂ ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም። የኢትዮ-ኤርትራ እርቅ በራሱ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅም ነበር ነገር ግን እኛ የትግራይ ልጆች አላገዝነውም ቅንነት ይጎድለናል ስለዚህ የትግራይ ህዝብን ጭንቅ ውስጥ ለማስገባት ስለሚፈልጉ ነው እንጂ የትግራይ ህዝብ እና መንግስት እልክ ውስጥ መግባት ሳይሆን የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅመው ነገሩን ወደ መልካም መቀየር ይችል ነበር። በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብን ሆን ብለው ስጋት ውስጥ ማስገባት አግባብ አይደለም ሰው የራሱን አቋም እንዲይዝ ቢደረግ የትግራይ ህዝብ በሰላም ከሌሎች ጋር እንዲኖር ማድረግ ይቻል ነበር ግን ሆን ተብሎ ማጨናነቅ እና ስጋት ውስጥ እንዲኖር የተለየ ሃሳብ የሚያቀርብ ባንዳ ብሎ መሰየም ይሄ የትም አያደርስም ለትግራይ አይጠቅምም የትግራይ ህዝብ መቼም ጠባብ ሆኖ አያውቅም ዛሬም ወደፊትም ኢትዮጵያዊ ነው ከጊዝያዊ ጥቅም በዘለለ አርቆ ማሰብ የሚችል ህዝብ ነው ስለዚህ ይህንን ህዝብ የሚጎዳ ስራ የሚሰራ መንግስት አይደለም ዶ/ር አብይ።

አውሮፕላን እና መብራት ከትግራይ ህዝብ ይቋረጣል ተብሎ የተወራው ሃሰት ነው ሆን ተብሎ ህዝቡን ለማስጋት ዶ/ር አብይ ጠላትህ ነው ለማለት የሚፈልጉ አካላት ናቸው ይህንን ወሬ እያናፈሱ የራሳቸውን ጥቅም የሚያካብቱት እንጂ ከህዝብ ጋር ጥላቻ ያለው መንግስት የለም ችግሩ የፖለቲከኞች ፈጠራ ጥላቻ ነው። #እውነታው_ይህ_ነው!
ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው!!!

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም" ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ‼

Post by Ejersa » 28 Dec 2019, 21:26

Ejersa wrote:
28 Dec 2019, 21:14

Post Reply