Page 1 of 1

በወላይታ ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ከህወሓት ተልዕኮ የተሰጣቸው ሆዳሞች!!!!

Posted: 21 Dec 2019, 00:24
by Hameddibewoyane
በወላይታ ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ተልኮ ከተሰጣቸው ስድስት (6) ሰዎች ውስጥ 6ኛ ላይ የተጠቀሰው አንዱዓለም ታደሰ የተባለው የዎብን አመራር ከትላንት ወዲያ ማታ #ደኢህዴን የዞኑን መስርያ ቤት ሊያቃጥል ሲል እጅ ከፍንጅ ተይዟል የሚል መረጃ ደርሷል። ሰውዬው የታሰረበትን ምክንያት አንድ የወላይታ ምናምን የሚል ገፅ እንዲህ በመቀባጠር ለማድበስበስ ሞክሯል። ውሸት ነው! እሱና የተቀሩት አምስቱ ሰዎች እልም ያሉ የህወሓት ተላላኪዎች ናቸው!! አሁን የጀመሩትን ነገር እንደሚያደርጉ 1, 2, 3, 4 ግዜ ፅፌያለሁ። እውነታው ይሄ ነው‼

በዚህች አጭር ጽሑፍ አንዱዓለም ለምን ለእስር እንደተዳረገ እንዳስሳለን። ነገሩ በአጭሩ እንዲህ ነው። አቶ አንዱዓለም ከነ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ሙላቱ ገመቹ ጋር ለስብሰባ ወላይታ ሶዶ ይመጣል። ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ያረፈውም ሌዊ ሆቴል ነበር። ስብሰባው ካለቀ በኃላ ወደ አዲስአበባ ሳይመለስ ትላንት አርብ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ ነበር። የሱ ሀላፊነት እንደ ዎብን ፓርቲ ሀላፊነቱ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግና በሰልፉ መያዝ ያለበትን መፈክር ማስተካከል ነበር። በዚህ መሀል ሀሙስ ቀን እሱ ያረፈበት ሆቴል ሌዊ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ቁርስ ልበላ ይመጣና አንዱዓለምን ያገኘዋል። ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው አንዱዓለምን ለምን ወደ አዲስአበባ እንዳልተመለሰ ይጠይቀዋል። የአንዱዓለም ምላሹ ወላይታ ቤተ ነውና የት እመለሳለሁ የሚል ነበር። በተጨማሪም ለአርብ ቀን ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይነግረዋል። ዶ/ር ጌታሁንም አርብ ቀን ምንም አይነት ሰልፍ እንደማይኖር ይገልጽለታል ምክንያቱም ኮማንድ ፖስቱ ስለማይፈቅድ ወደ መጣህበት ተመለስ ይለዋል።

አንዱዓለም እኔ የትም አልሄድም ኮማንድ ፖስቱም ቢሆን ህገወጥ ነው የሚል ምላሽ ይሰጣል። ሰልፉም እንደሚደረግ በደንብ ይነግረዋል። በንግግራቸው መሀል አንዱዓለም ወላይታ በአንተ አይነቱ ደካማና ህዝብን ለእንጀራ በሚሸጥ መመራቱ ያሳዝነኛል ይለዋል። ከዚህ በኃላ ጌታሁን በጣም ይናደድና እኔን አልተረዳህምና የጥበቡ ቢሮ ብትመጣ በሰፊው እናወራለን ይለዋል። ስለዚህ ቢሮ መጥተህ አለመግባባቶችን እንፍታ ይለውና ይለያል። አንዱዓለምም ትንሽ ቆየት ብሎ ጥሪውን አክብሮ ለውይይት ጥበቡ ቢሮ ይሄዳል። በመሀል ቢሮ ውስጥ ማንም ሰው አልነበረምና ሶፋው ላይ ቁጭ ብሎ ጥበቡን፣ ዳጋቶንና ጌታሁንን ይጠብቃቸዋል። ሲቆዩ ስልክ ይደወልለትና ለማውራት ከቢሮ ወደ ውጭ ወጣ ይላል። በዚህ መሀል እዛ ግቢ ውስጥ ቡና የምታፈላ ልጅ ሶፋው ላይ እሳት ትሎክሳለች። ሶፋው መንደድ ስጀምር ጥበቃው ጥይት ወደ ሰማይ መተኮስ ይጀምራል። በዚህ መሀል ግርግር ይፈጠራል። የዞን ፖሊሶችም ይህን ያደረገው አንዱዓለም ነው ብለው ወደ እስር ቤት ወሰዱት። እሱን ያሰረው በጌታሁን የሚመራው የዞን ፖሊስ እንጅ ኮማንድ ፖስት አይደለም።

እና ድራማው በጣም የወረደ፣ ደራማውን የጻፈውን አካል አቅም የሚያሳይና ተራ ነበር። አንድ ግለሰብ በህግ የተላለፈው ነገር ካል ደረጃውን በጠበቀ መንገድ መጠየቅ ይቻል ነበር። ግን የሆነው የማይመጥን ምንአልባት የአገራችን በፖለቲካው ዘርፍ የሞራል ዝቅጠትን አመላካች ነው። ስለዚህ ሁለም ሰው ይህንን ነገር ማውገዝ ይጠበቅበታል። የዞን አመራሮችም በአስቸኳይ እንዲፈቱት እንጠይቃለን።