በውይይቱ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በመቀለ ዩኒቨርስቲ የትግራይ ተወላጆች ምሁራን ከባድ ተቋውሞ ገጥሟቸዋል።
የመቀለ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የትግራይ ተወላጆች ምሁራን ውይይት ላይ መነሻ ፅሕፍ ያቀረቡት ሜጀር ጀነራሉ የትግራይን ሉእላዊነት ኣስፈላጊነት ላይ በሰፊው ኣቅርበዋል።
ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሐን ወልደአረጋይ ንግግራቸውን እንደጨረሱ በውይይቱ የታደሙት የትግራይ ተወላጅ ምሁራን በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ያነነሷቸው ጥያቄዎች እንዲህ የሚሞግት ነበር!
(1).አንተ በስልጣን በነበርክበት ወቅት የትግራይ ጥቅም የሚከበረው በኢትዮጵያ ብቻ ነው ስትል ነበር ፤ አሁን ደግሞ ከስልጣን እንደተባረረክ በሳምንታት ውስጥ የትግራይ በኢትዮጵያ መቆየት ብዙ ችግር እንደሚያጋጥማት መናገር ጀመርክ ፤ ይሄ ከግል ጉዳይህ ጋር የተያያዘ አይመስልህም?
(2). ትግራይ የድህነት ሞዴል የሆነችው በእናንተ እንጂ በማን ሆነች እና ነው? የትግራይ ህዝብ ድህነት በአንድ አመት ውስጥ በአብይ አህመድ የተፈጠረ ነው እንዴ?
(3). ባለፈው ሳምንት የትግራይ ሉእላዊት ሀገር በትንሽ መስዋዕትነትም ቢሆን እውን መሆን አለባት ብለሀል ፤ ትንሽ መስዋዕትነት ማለት ስንት ነው .? በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ ልጆቻችሁና ሚስተቶቻችሁ እዚህ መስዋዕትነት ለመሆን ይመጣሉ ? የሚሉ ትችቶች ተስተናግደዋል !!
Sulyiman Abdel
