Page 1 of 1

መምህር አብርሃ ደስታ በእስር ቤት ሁኖ የእኔና የህወሓት ክርክር ዛሬ ቀን 8:00 ሰአት ላይ ተከታተሉት እያለን ነው! እንግዲህ ተከታተሉት!!!!

Posted: 20 Dec 2019, 09:03
by Hameddibewoyane
የዓረና አባል ከመሆን ግን የአብን አባል መሆን የተሻለ መስሎ ተሰማኝ!

በሁለት
ምክንያት
1ኛ አብን ህወሓት አሸባሪ ነው በህግ መታገድ አለበት። ምክንያቱም በራሱ ህግ የማይገዛ አሸባሪ ድርጅት ነው ብሎ ያምናል።

2ኛ ወደ ምርጫ መቅረብ የለበትም ምክንያቱ በዴሞክራሲ በምርጫ የማያምን የማይቀየር የማይለወጥ ቁሞ ቀር ድርጅት ስለ ሆነ ይላል !!

ዓረና ትግራይ አይደለም ለህወሓት አሸባሪ ብሎ ሊከሰው በህወሓት አዳራሽ ሁኖ በታፈነ አዳራሽ ድምፁ አይደለም ወደ ትግራይ ህዝብ ሊደርስ እስከ አዳራሹ በር በማይደርስ ከህወሓት ቁሞ ቀር ቁጭ ብሎ ይከራከራል! ያሳዝናል! ትናትና የዓረና አመራሮች አብርሃ ደስታ ጭምር እሱና ጓዶኞቹ በምስል እያሳዩ የህወሓት ካድሬዎች ስለ ሰብሰባው ዜና እየሰሩ አመሹ! ህዝብኻ ምዳል እዚ እውን የጠቓልል እዩ!

ምስኪኑ አብርሃ ደስታ በታፈነ የመቆዶንያ ሆቴል አዳራሽ ሁኖ የህወሓት እና የዓረና ክርክር 8:00 ተከታተሉ ይለናል ። አዘሳዛኝ ! የተዘጋ በር ሳያስከፍቱ በተዘጋ ቤት ክርክር ያደርጋሉ !!

ትዝ ያለኝ ነገር ልንገራቹ
አማኑኤል መስፍን የተባለ የግእዝ ምድያ ባለቤት በትግራይ ወረዳዎች በተለይ በመቐለ 70 እንደርታ ወረዳዎች አካባቢ በቀጥታ ስርጭት የህዝብ እሮሮ ቦሶት ወደ ህዝብ ሲያስተላልፍ የህወሓት አመራሮች ደንግጠው ከትግራይ እንዲወጣ ተደረገ ልጁ የግሉ ምድያ ዘግቶ ወደ ግሉ ስራ ተሰማርተዋል። አብርሃ ደስታ ይህንን ጉዳይ እያወቀ በዝምታ አልፎ ዛሬ ብቻው በታፈነ አዳራሽ ሁኖ ለህወሓት ካድሬዎች ድምፁ ሊያሰማ ነው ክክክክክክክ"

አክቲቪስት ሚኪ ተስፋዬ የአረና አባል ከ አዲስ አበባ