Breaking News: በዎላይታ ዞን ነገ 10/04/12 ዓ ም ሁኔታ በተመለከተ ከኮማንድ ፖስት የተሰጠ ሙሉ መግለጫ!!!!
Posted: 19 Dec 2019, 12:33
ነገ በዎላይታ ላይ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሌለ በአከባቢው ያለው ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ገለፀ። ኮማንድ ፖስት በዎላይታ ባለው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።
ዛሬ በዎላይታ አከባቢ ያለው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ነገ ታህሳስ 10/12 ዓ ም ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይደረግ አስተውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መንገዶች ነገ ሰላማዊ ሰልፍ አለ በሚል በግለሰቦች እየተነገረ ያለው ህጋዊ ፍቃድ የለለውና ኃላፊነት የሚወስድ አካል የለለው በመሆኑ ህዝቡ የሚከተለውን መመሪያ እንዲከተል መግለጫ ተሰጥቷል።
1 - ነገ ማንም ከመደበኛ መከላከያ ሠራዊት ውጪ ማንም የሠራዊቱን ደንብ ልብስ መልበስ አይቻልም።
2 - በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
3 - በዎላይታ በሁሉም ቦታ ዛሬ ማታ ከ12 :00 ጀምሮ ነገ ቀን ሙሉ ባለሁለት እግር ባጃጅ ከተማ ውስጥ ማሽከርከር በፍጹም አይቻልም።
4 - በማህበራዊ ሚዲያ ሆነ በሌላ መንገዶችም ህዝብን ለግጭትና ለሰልፍ መጥራት አይቻልም።
5 - ሥራዊቱ የህዝብን መብት ሰጪም ከልካይ ስላይደለ ህዝቡ በሠራዊቱ ጎን መቆም እንዳለባቸው።
6 - ነገ ህዝብ ህገመንግስታዊ መብት ጥያቄዎቻቸው በህገወጥ መንገድ ታፍኗል በሚል በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ውይይት አድረገው በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከታቸው አቤቱታ እንዲያቀርቡ ተፈቅዷል።
7 - ነገ በዎላይታ ከማለዳው ጀምሮ በሁሉም ቦታ እስከ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ እንዲቆዩ ተብሏል።
በአጠቃላይ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ሳይጋጩ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያቀርቡና ነገ በሁሉም ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይቻል የኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ኮለኔል ተስፋዬ ሀጎስ ጥሪ አቅርቧል።