Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የአልባንያ ተቃዋሚዎች በትግራይ! BBC አማርኛ!!!!

Post by Ejersa » 19 Dec 2019, 07:37

ምናልባትም የ'ትግራይዋ አልባንያ' ያለምንም የአቋም ለውጥ ለረዥም ዓመታት የህወሓት ተቃዋሚ መሆኗ ከቀሪው የትግራይ ክፍል የተለየች ሊያስብላት ሲችል፤ አልባንያም በአስቸጋሪ መልክዓ ምድሯ እንዲሁም በውስብስብ የታሪክ፣ የባህልና ማህበራዊ ሁኔታዎች ተለይታ የምትኖር መሆኗ ካላመሳሰላቸው በስተቀር ከመቐለ በስተምሥራቅ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውና ቀድሞ በእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ስር የነበረችው 'እግሪ ሃሪባ' በብዙዎች ዘንድ 'አልባንያ' በመባል ትጠራለች። ይህ ግን በሌላ ሳይሆን፤ ይደርስብናል የሚሉትን ኢፍትሀዊነት አምርረው በመቃወማቸው፣ በደል የሚሸከም ጫንቃ የለንም በማለታቸው መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢዋ ነዋሪዎች ያስረዳሉ። ልዝርዝሩ :arrow: :arrow:
https://www.bbc.com/amharic/50818734?oc ... tytckNZ4NE