Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 41950
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ! ጋዜጠኞች ከፖለቲካ ይቆጠቡ !!! መረጃ ዕውቀት አይደለም !!!

Post by Horus » 18 Dec 2019, 02:30

ይህ አባባል የተተረተው (የተነገረው) አለ ምንም ትምህርት፣ ጥናት፣ ምርምር፣ እና እውነት (ፋክት)፣ ይህ ሆነ፣ ያ ሆነ፣ እሱ እንዲህ ነው፣ ይህ ሊሆን ነው ፣ ያ ሊከሰት ነው ለሚሉ ላልተማሩ፣ ተናጋሪ እና ደምዳሚዎች ነው ።

በእውቀት ሳይንስ ውስጥ፣ የዕውቀት መሰላል ወይም ፒራሚድ የሚባል እውነታ አለ። ይህ ፒራሚድ 5 ደረጃ አለው ።
እነሱም ከላይ ወደ ታች እንደ ሚከተለው ነው።

5ኛው ጥበብ ይባላል፤ 1%
4ኛው ግንዛቤ ይባላል፣ 9 %
3ኛው ዕውቀት ይባላል። 20%
2ኛው መረጃ ይባላል፣ 30%
1ኛው ምልክት ይባላል። 60%

እጅግ ዝቅተኛው ዳታ ወይም ድርጊት ይባላል። በፊደል፣ በሰዕል፣ በቁጥር የምናመለክተው ዛፍ፣ሰው፣ ሜዳ፣ ጨው ብለን በስም ወይም በምልክት ግንአ ዳታ ነው።

ይህ ዳታ የዕውቀት ሁሉ 60% ነው።

ቀጥሎ የሚያድገው መረጃ ነው ። እሱም ኢንፎርሜሽን የሚባለው ነው። ያ ደሞ የዕውቀት ሁሉ 30% ነው። ለምሳሌ ጋዜጠኞች ሁሉ ያላቸው እውቀት ወይም ለሕሽቡ የሚያሰራጩት ዕውቀት መረጃ ሲሆን እሱም ከዝቅተኛ ዳታ ቀጥሎ ያለ የእውቀት አይነት ነው።

ይህም ምን ሆነ፣ ማ፣ ዬት፣ መቼ፣ ወዘተ ለሚሉት መልስ የሚሰጥ የዕውቀት ደረጃ ነው።

3ኛው እውቀት ነው ። እሱም የማወቅ 20% ነው። እውቀት አንድ ነገር ምን እንደ ሆነ ከመንገር አልፎ፣ አንድ ነገር እንዴት እንደ ሚሰራ፣ እንደ ሚደረግ ማወቅ፣ መቻል ማለት ንው። ለዚህ የበቁ 20% ናቸው ማለትም እጅግ ባደገ ማህበረሰብ ።

4ኛው ግንዛቤ (መግባት) ወይም አንደርእስታንዲንግ) ይባላል ። ይህ አንድን ነገር በውስጡ ሆኖ እንደ ራሱ ማወቅ ማለት ነው። በዚህ ብቃት የሚያውቁ ከፍተኛ ሳይንቲስቶች፣ ተመራማሪዎች ነው ። አንድ ነገር ገብቶኛል ማለት ዝም ብሎ በልማድ እንደ ምባለው ሳይሆን ሙሉ እውቀትን ይጥይቃል ።

5ኛው ጥበብ ወይም ዊዝደም ይባላል። ባንድ ያደገ ህብረተሰብ ውስጥ ጠቢብ ወይም ዋይዝ የሚባሉ ሰዎች 1% አይደርሱም። ለምሳሌ አንድ መሪ ታላቅ ለመባል ጠቢብ ወይም ዋይዝ መባል መሆን አለበት ።

እንግዲህ ባገራችህን እንደ ትልቅ ነገር የሚታዩት ጋዜጠኞች 2ኛ ደረጃ መረጃዎች ናቸው ። የእውቀት ደረጃ እንኳ አልደረሱም ።

የፓርቲ መሪ የሚባሉትም ቢበዛ ከእውቀት (3ኛ) ድረጃ ያላለፉ ናቸው።
Last edited by Horus on 19 Dec 2019, 03:43, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 41950
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ! ጋዜጠኝች ከፖለቲካ ይቆጠቡ !!! መረጃ ዕውቀት አይደለም !!!

Post by Horus » 18 Dec 2019, 03:07

እንግዲህ 5 የእውቀት አይነቶችን ይዘን ፖለቲካ የሚሰራው በየትኛው እውቀት ነው ብንል? ትክክለኛ ሚዛን፣ ፍትሃዊነት፣ ሞራል ብቃት፣ ህጋዊነት፣ ወዘተ የሚባሉት እውቀቶች ጥብብ ወይም ዊዝደም ይባላሉ ። ዛሬ በዚህ እውቀት ውስጥ ያሉ የኢዮጵያ ፖለቲካ መሪዎች በጣት ይቆጠራሉ ። ለዚህ ነው ፖለቲካችን በቅውስና ምስቅልቅልነት ፣ ወስብስብነት ተቀርቅሮ ያለው !!

Horus
Senior Member+
Posts: 41950
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ! ጋዜጠኝች ከፖለቲካ ይቆጠቡ !!! መረጃ ዕውቀት አይደለም !!!

Post by Horus » 18 Dec 2019, 03:33

ለምሳሌ ይህን ዜና ስሙ።

ይህ ዜና ትክክል (ዳታ ወይም ፋክት) ከሆነ ስሙ መረጃ ወይም ኢንፎርማኤሽ ይባላል ። እውቀት አይደለም ። ጌታቸው ሞተ የሚለው ሌላ አንድ ነገር እንዴት እንደ ሚሰራ መሰረት ሊሆን ይችላል ግ ን ራሱ አንድ ነገር እንዴት እንደ መደረግ የሚመራ እውቀት ወይም ክህሎት አይደለም ።


Horus
Senior Member+
Posts: 41950
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ! ጋዜጠኝች ከፖለቲካ ይቆጠቡ !!! መረጃ ዕውቀት አይደለም !!!

Post by Horus » 18 Dec 2019, 04:15

ለምሳኤ ይህን የፍቅሬ ቶሎሳ ቪዲዮ ወሰዱ ። በእኔ ግምት የፍቅሬ መጽሃፍ ባብዛኛው ስህተት ነው ማለትም ዳታው እና መረጃው ማለት ነው። ግ ን ፍቅሬ የሚያራምደው ጽንሰ ነገር ዊዝደም ወይም ጥበብ የሚባለው ነው ። ለምን ቢባል ሃሳቡ አላማ አለው፣ ወደፊት የሚፈተረውን አስከፊ ነገር ለመግታት ወዘተ በአርቆ አስቢነት ስለመመደብ ነው ።


Horus
Senior Member+
Posts: 41950
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አበሻ በአፉ ጤፍ ይቆላል ! ጋዜጠኝች ከፖለቲካ ይቆጠቡ !!! መረጃ ዕውቀት አይደለም !!!

Post by Horus » 19 Dec 2019, 02:32

እንደ ገና ልድገመው ፤

ያቢይ መንግስት ስልጣን ከወሰደ ጀምሮ ብዙ፣ ብዙ የሚዲያ ቡድኖች ተፈጥረዋል ። ይህ በጣም ደስ የሚል ነገር ነው።

ግን አንድ ነገር መከታተል አለብን ። አንድ ነገር ሳይሆን ሆነ የሚሉ መረጃ ሳይሆን ዳታ ወይም ፋክት እንኳን የላቸውም ። ይህ የመጀሪያው አሳፋሪ ነገር ነው።

ሁለተኛ ፣ እነዚህ እንደ አሸን የፈሉት ታናንሽ ዲጂታል ሳንቲም መልቀኒያ ሚዲያዎች ብዙዎቹ ተመሳሳይ ዜና ነው ሚያሰራጩት ።

የተለያየ መረጃ ወይም ኢንፎርሜሽን የሚያቀርቡትም ቢሆኑ ዛው ያይዳቸው ኢንፎርሜሽን ማስተጋባት ነው። ማን ምን አረገ? ምን የት ተደረገ ውዘተ ።

አንዳቸውም የኢትዮጵያ ችግር ምንድን ነው የሚለውን ችግር አፈላላጊ አይደሉም።

አንዳቸውም ለታወቁት የስራት ችግሮችን መፍትሄ ለመቅረጽ ፍላጎትም፣ ችሎታም፣ ብቃትም የላቸውም ።

ባንድ ቃል ተራ ጋዜጠኝች ለማህብረ ሰቡ የንድፈ ሃሳብም ሆነ፣ የክህሎት እውቀት አይሰጡም ።

ለዚህ ነው ከፖለትካ ተቆጠቡ ያልኩት !!

በፖለቲካ ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ በፖለቲካ ክህሎት ወይም እስኪል እና በፖለቲካ ትግበራ የሰለጠኑ እና ብቃል ያላቸው ደሞ እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ፖለቲካዊ ምሁር ወይም የፖለቲካ ባለ ሙያ ሆነው በትክክል መስራት ግድ ይላቸዋል ።

የፖለቲካ ተንታኞች እንደ ተመስገን ያሉት ጋዜጣ ተጠቀሙ እንጂ ስራቸው አንድ የፖለቲካ ባለ ሙያ፣ ተንታኝ እና ተሟጋች የሚሰራውን ነው ሚሰሩት ። የነዚህ ምደባ ይለያል ።

Post Reply