Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

"ትግራይ ውስጥ ሁሉም በሚያስብል አብይ በሚባል በሽታ ታሟል!!!!

Post by Ejersa » 16 Dec 2019, 12:09

ትግራይ ውስጥ የገባ በሽታ አለ።
በዶክተር አብይ መናደድና መሳደብ
ወደ ውጪ ሲሄድ (ለሽርሽር) ወጣ ይላሉ
ሲናገር ይናደዱና (ሰባኪ) ነው ይሉታል
መኪና ሲነዳ (ለፎቶ) ነው ይላሉ
ሲሸለም (በፍጹም አይገባውም) ይላሉ
ወደ ታች ወርዶ ከሰዎች ጋር ሲገናኝ ክብሩን አይጠብቅም (መሽረፈት) ይሉታል ይናደዱበታል
በገበሬዎች ማሳ ገብቶ እህል ሲያጭድ ይናደዳሉ( የትግራይ ገበሬ አብይ እህልህን ሊቀማህ ነው) ይሉታል
አረንጓዴ ዘመቻ መሰረቱ ችግኝ ነው ብሎ ውሃ ሲያጠጣ ሲያዩት ይናደዳሉ (ጊዜ በዝቶት) ይላሉ
በእንግሊዝኛ ሲናገር ይናደዳሉ (ፎቶ ሾፕ) ነው ይላሉ
ኤርትራና ኢትዮጵያ ሰላም እንዲኖራቸው ሲጥር ይናደዱና(የሆነ ነገር አስቦ ነው) ይላሉ
እርዳታና ብድር ሲያመጣ ይናደዳሉ(ሃገር ሸጣት ይላሉ)
እውነታቸው ነው የሚካኤል ቤተክርስቲያን ቄስ "ትግራይ ውስጥ ሁሉም በሚያስብል አብይ በሚባል በሽታ ታሞ ስላለ ፀበል እየረጨን ነው የምንውለው" ሁሉም ስራውን ትቶአል።
የስነ አእምሮ ችግር ደርሶብን ነው ያለው። የፌደራል መንግስት እገዛ ካላደረገልን ብዙ ሰው አብይ በሚባል በሽታ እንደሚታመም አልጠራጠርም ብለዋል።
እኔ ደግሞ አብይ የሚባል በሽታ ምን እንደሆነ አላውቀውም በዚህ ሰውዬ ሰበብ ግን እንዳያመኝ እጠራጠራለሁ ብለዋል።
"በእውነት ታመናል ዶክተር ፣ተማሪው፣ሰራተኛው፣ፖሊስ፣ጋዜጠኛ ቄሶች በሙሉ አብዛኛው ያልታመመ የለም ከገበሬው በስተቀር ወይ ያገኘነው ጣጣ"