Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የአብዲ ኢሌ ርዝራዦችና የህወሃት ወኪሎች የሶማሌ ክልልን ለማተራመስ እየተዘጋጁ ነው!

Post by Ejersa » 16 Dec 2019, 12:02

ህወሃት ሶማሌን የፈጠረው ይመስል ህወሃት ከሌለ ሶማሌ ይጨፈለቃል የሚል የቅዠት እና መያዥ መጨበጫ የሌለው በፌድራሊዝም ስም የሚነዛ ፕሮፖጋንዳን በማጮህ የአቢዲ ኢሌ የማፍያ ሥርዓት ርዝራዦች ከህወሃት ወኪሎች ጋር ተጣምረው በሶማሌ ክልል መሪ ሙስጠፋ ዑመር እና በሌሎች የክልሉ አመራሮች ላይ የስም ማጥፋት የፕሮፖጋንዳ ለማድረግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም በጋዜጠኝነት ስም የህወሃት ወኪልና ተባባሪወች የሆኑት እነ ፋኑኤል ክንፉ ናይሮቢ ድረስ በተዘረጋ መረብ ተመሳሳይ ፕሮፖጋንዳ ሞክረው ውጤት ባያመጣላቸውም አሁን እንደገና በአዲስ መልክ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። ፕሮፖጋንዳው ከወሬ ባለፈ ዓላማው የክልሉን ሰላም በመረበሽ የለውጥ መሪ ሆነው ውጤት ያመጡትን ሙስጠፌ ዑመርና ቡድናቸውን ከስልጣን በማስወገድ ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር የማይግባባ ተቃዋሚ ቡድን በግርግር እንዲመጣ ነው።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዶክመንተሪ እስኪሰሩበት ድረስ ዘግናኝ በሆነ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም የነበረው ህወሓት ለሶማሌ ክልል ሕዝብ እቆረቆራለሁ ብሎ ቢያወራ አድማጭ ባያገኝም የህወሃትን ወንጀል ሲያስፈጽሙ የነበሩ የአብዲ ኢሌ ርዝራዦች ግን አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ የአመጽ ቅስቀሳና ስም የማጥፋት ፕሮፓጋንዳወችን ተያይዘውታል።

እነዚህ ከግላቸውና ከቡድናቸው ጥቅም ውጭ የክልሉ ሕዝብ ደህንነትና ብልጽግና ቅንጣት ያክል የማያሳስባቸው ቡድኖች የሶማሌ ክልል ከአብዛኞቹ የሃገራችን ክልሎች በተሻለ መልኩ ሰላማዊ መሆኑ ስለረበሻቸው ውዥንብር በመፍጠር ክልሉ ችግር ውስጥ ያለ ለማስመሰልና ህዝቡ መሪዎቹ ላይ ጥርጣሬ እንዲኖረው እውነት የሚመስሉ የሀሰት መረጃወችን በማቀናበር ዶክመንተሪወችን አዘጋጅተው በቀጣይ ቀናት መጠነ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ ለመክፈት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል።
Brook Abegaz