Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ሚስጢር ሲገለጥ፤

Post by Hameddibewoyane » 16 Dec 2019, 09:17

ባለፈው ኣርብ በዋልታ ቴሌቪዥን የፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣው የደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ተከትሎ የመላ የኣገራችን ህዝብ ላይ ድንጋጤና ኣግራሞት መፍጠሩ ይታወሳል፡፡ እንደሚታወቀው የተሰራጨው መረጃ ወድያዉኑ ከዋልታ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንዲጠፋና በማረምያ መረጃ እንዲተካ የተደረገ ሲሆን ቀጥሎም የቴሌቪዥን ጣብያው የበላይ ሃላፊዎች በሰጡት ማብራርያ ጉዳዩ ከእውቅናቸው ውጭ እንደተፈፀመና ይህን የመሰለ የተቀነባበረ የፈጠራ ወሬ ሊነዛ የሚፈልግ የኣገራዊ ለውጡ ተቃዋሚ የሆነ ሃይል እንደሚሆን ፍንጭ ሰተዋል፡፡

የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶው ከተሰማበት ቅፅበት ጀምሮም ብዙ ሰው ስለጉዳዩ መረጃ ሲሰበስብ፣ ሃሳብ ሲያብላላና ትንበያዎች ሲለዋወጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ እኔም በበኩሌ የድርጊቱ ኣላማ ምን ሊሆን እንደሚችልና ፈፃሚዎቹ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃ ሳሰባስብና ከብዙ ሰዎች ጋር ሃሳብ ስለዋወጥ ቆይቻለሁ፡፡ ዋልታ ቴሌቪዥንም ስለ ድርጊቱ እወነተኛ መረጃ እስኪያቀርብልንና ህጋዊ እርምጃው እስኪያሳውቀን ድረስ እንሆ ኣንድ የድርጊቱ ፈፃሚ ኣካል ከፍተኛ ትንበያና ሁለት ድርጊቱ እንዲፈፀም ያስፈለገበት ኣሳማኝ ኣመክንያዊ-ኩነቶች/Reasonable-Scenarios፡-

የድርጊቱ ፈፃሚ ኣካል ከፍተኛ ትንበያ፡-

ይህን የፈጠራ ወሬ የመንዛት ተግባር ማን ሊፈፅመው ይችላል ለሚለው ጥያቄ መልሱ የህወሓት የበላይ ኣመራሮችና ደጋፊዎች ናቸው፤ ለዚህም ሁለት ኣበይት ኣመክንያዊ-ኩነቶች/Reasonable-Scenarios ኣሉ፤

ኣመክንያዊ-ኩነት ኣንድ፤

የዚህ ተግባር ኣንደኛው ኣመክንያዊ-ኩነት የሚመነጨው የኢህኣዴግ የውህደት ኣጀንዳና የኣዲሱ የብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ህወሓት ወደ ብልፅግና ፓርቲ ለመቀላቀል እግሩ እንደማያነሳና ልዩነቱ ይዞ እንዲሚታገል ኣሳውቆዋል፡፡ ይህም ተከትሎ በህወሓት ውስጥ ታላቅ ውጥረትና ልዩነት ነግሷል፡፡ የውጥረቱና የልዩነቱ መንስኤም ዶ/ር ደብረፅዮንና እሳቸው የሚመሩት ህቡእ ቡዱን በመጨረሻ ያቀረበው የኣማራጭ ሃሳብ ሲሆን ሃሳቡም ቀርበን መደራደርና ለውጡን መደገፍ ኣለብን የሚል መሆኑን ጭምጭምታዎች በሰፊው ይወራሉ፡፡

ይህ የዶ/ር ደብረፅዮን ከግል ባህሪያቸው የመነጨ ተቀራርቦና ተደራድሮ ለመስራት የመፈለግ ግልፅ ኣቋም ተከትሎም ከለውጡ ሃይሎች የተለየ ትኩረትና ማባበያ እየጎረፈላቸው እንደሆነ የሚስተዋልና በሰፊው የሚወራ ጉዳይ ከሆነ ሰነባብተዋል፡፡ በዚህ መንገድም የለውጡ ሃይል ዶ/ር ደብረፅዮንን ነጥሎ በማግባባት ህወሓት ካለተሰሚ መሪ ማስቀረትና በስተመጨረሻም ድርጅቱ እዚህ ግባ የማይባል ሃይል ሆኖ እንዲከስም ለማድረግ የታሰበ መሆኑ ለሁሉም ግልፅ ነው፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮንም በበኩላቸው በተጨባጭ ያልተቆጣጠሩትን የይስሙላ ስልጣን ይዘው ግዜው ያመጣው ሸክም እላያቸው ላይ በመከመሩ የተሰላቹና ተስፋ የቆረጡ በመሆኑ ከዚህ ስንክሳር ተላቅቀው እፎይ ማለት እንደሚፈልጉ ይታወቃል፡፡

በተቃራኒው ይህ የዶ/ር ደብረፅዮን ኣቋም ያወቁና ከለውጡ ሃይሎች ጋር የከረረ ጥልና ፍጥጫ ውስጥ ያሉት የህወሓት ኣመራሮች ዶ/ር ደብረፅዮን ጥሏዋቸው ሊሄዱ እንደሚችሉና እንደዛ ከሆነም እሳቸውን የሚተካ መሪ ማግኘት እንደማይችሉ ስለሚያውቁ “በዚህ ኣስቸጋሪ ግዜ ጥለሀን ለመሄድ የምትወስን ከሆነ የሃይል እርምጃ እስከመውሰድ እንደርሳለን” በማለት ኣስፈራርተው ሊያቆዩዋቸው መወሰናቸው ኣንዳንድ ከድርጅቱ ሾልከው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለሆነም ኣገራዊ ለውጡን ኣምርረው የተቃወሙ የህወሓት ኣመራሮችና ደጋፊዎች የዋልታው የማስፈራርያ የፈጠራ ሞት መርዶ ለማሰራጨት ወስነው በዝግጅት ላይ ቆይቷል፡፡

ኣመክንያዊ-ኩነት ሁለት፤

ሁለተኛው የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ የመንዛት ኣስፈላጊነት የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ልክ ይህንን የፈጠራ ወሬ ከመሰራጨቱ በፊት በትግራይ የፌስቡክ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ይዞ የቆየ ኣንድ ከዚህ በፊት ያልታየ ከባድ እንቅስቃሴ ነበር፡፡

ይህ እንቅስቃሴም በትግራይ ደረጃ የተንሰራፋውና መላው የትግራይ ህዝብ ያቆሰለ የኣንድ ኣከባቢ የበላይነትና ፈላጭ-ቆራጭነት ከፍተኛ ተቃውሞ ለማስተናገድ የተገደደበት ልዩ ኣጋጣሚ ነው፡፡

ይህም የህወሓት ኣገዛዝ በትግራይ ደረጃም “ኣፓርታይድ” ሊባል በሚችል ደረጃ ስልጣን በኣንድ ጎጥና ዘረኛ የስልጣን ኔትወርክ መወረሩ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ጠንክሮና ፍርጥርጡ ወጥቶ ለኣደባባይ ተቃውሞ በመብቃቱ ለህወሓት ካድሬዎች ከፍተኛ የራስ ምታት ሆኖ በኣጠቃላይ ክልሉም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ ኣድርጎታል… ኣሁንም ቢሆን ተቃውሞው በቀጣይነት እየጋለ በመሄድ ይገኛል፡፡
ይህ የኣንድ ሰፈር የበላይነት ችግር በመላው ትግራይ በሰፊው የሚሰተዋል ቢሆንም ይህ የሰሙኑ ተቃውሞ ግን ራስን-በራስ የማስተዳደር መብት ፍፁም ከተገረሰሰባቸው ኣከባቢዎች ኣንዱ የሆነው የተንቤን ወረዳ ላይ ኣተኩሮ የተቀስቀሰ ነበር፡፡

ነገርይዎም እንዲህ ነበር፤ በተንቤን ወረዳ የሚገኙ የፖለቲካ ሽማምንቶች የስርዓቱ ዋና ባለቤቶች ነን ብለው በሚመኩ የዓድዋና ኣከባቢው ካድሬዎች ብቻ መሆናቸው የወረዳው ሙሉ የኣመራር ሰንሰለት ከኣንድ ሰፈር በመጡ ካድሬዎች የተወረረ መሆኑን የካድሬዎቹ ሙሉ ስም ዝርዝር እስከማጋለጥ የደረሰ ተቃውሞ በኣብነት ቀርቦ ነበር፡፡ ይህም በትግራይ ውስጥ የኣንድ ኣከባቢ የበላይነት መኖሩና ስርዓቱ ኣይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ህዝብ እንኳን በእኩል ዓይን የማያይ መንደሬ-ስርዓት መሆኑን በማጋለጥ እስካሁን በጣም የበረታው ተቃውሞ እንዲደርሰው ተደርገዋል፡፡

ይህን ተከትሎ “ደም ከውሃ ይወፍራል” የሆነባቸው የመንደሬ-ስርዓቱ እንደ ኣዲስ የተሰባሰቡ ደጋፊዎች የኣልሞት-ባይ-ተጋዳይ መከታቸው ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል፡፡ ይህ ድርጊትም እንቅስቃሴው ወደ ኣልተገመተ ከፍተኛ ደረጃ የወሰደው ሲሆን በዚህ የተጋጋለ ተቃውሞ ውስጥም ቁጥር ኣንድ የተቃውሞ ሰለባ ለመሆን የበቃው የቀድመው የህወሓት ታጋይ፣ የመንደሬ-ስርዓቱ ኣባልና ቀድም ብሎ በቪኦኤ ትግርኛ በኣሁኑ ሰዓት ደግሞ በቢቢሲ ትግርኛ ዘጋቢ ሆነ እየሰራ የሚገኝ ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ኣለም-ኣቀፋዊ ስነ-ምግባር እንዲጠብቅ የሚጠይቀው ሞያውን ችላ በማለትና የህዝብ ጥያቄ በመናቅ ከህወሓት ኣመራሮች ተልእኮ በመቀበል ህዝባዊ ተቃውሞው ለመቀልበስ ማስቀየሻ የሚሆን ተራ የፈጠራ ወሬ ይዞ በመምጣት ለመሟገት ሞኩሮ ለህወሓት የቀን-ተቀን ክስተት የሆነውን መራራ ውድቀት ኣጋጥሞት ከፍተኛ ሞራላዊ ኪሳራ ሊድርስበት ችሎዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በፌስቡክ በፍፁም የራስ መተማመን የነዛቸው ወሬዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከፌስቡክ ገፁ ለማጥፋት እስከመገደድ ደርሰዋል፡፡ እንቅስቃሴውም ተጠናክሮ ቅጥረኛው ጋዜጠኛ የህዝብ ድምፅ ለማፈን ከህወሓት ጋር በመመሳጠሩ ይቅርታ እንዲጠይቅና ከተከበረው የጋዜጠኝነት ሞያው እንዲታገድ የፊርማ ማሰባበስብ ቅስቀሳዎች እስኪካሄዱበት ነገሩ ተካርሮ ይገኛል፡፡

በዚህ መልኩ ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ህዝባዊ ቁጣ መጠንና ጥንካሬ በየሰዓቱ እየጨመረ በመሄዱም ብዙ ሰው ከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት እንዲፈጠርበትን ትልቅ ኣጃንዳ እንዲሆን ተችለዋል፡፡ ይህም ለህወሓት እጅግ በጣም ኣደገኛ የሆነ ክስተት ለመሆን መብቃቱ ለሁሉም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ነጥሎ የኣንድ ሰፈር ኣመራር ኣድርጎ የሚወስን ህዝባዊ ትግል ለመቀልበስ የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ማሰራጨትና የህዝቡ ቀልብ ወደ ሌላ ኣቅጣጫ መዘወር ለኣንዳፍታም ይቆይ የማይባል እርምጃ ሆኖ ተገኘ፡፡

በስተመጨረሻም ይህ የፈጠራ ወሬ በዋልታ የፌስቡክ ገፅ እንዲሰራጭ የተመረጠበት
ምክንያት ሲታይ ዋልታ ኣሁንም በዋነኝነት የህወሓት ንብረት በመሆኑና ኣገራዊ ለውጡ እያስቀጠለ መሆኑ ቢታወቅም በተቋሙ ያሉት ሰራተኞች የህወሓት ቀንደኛ ኣባላትና ደጋፊዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህ ኣባላት በማግባባትና በጥቅማ-ጥቅም በመደለል ተግባሩ ሙሉ-በሙሉ በህወሓት ሰዎች ኣቀናባባሪነትና ፈፃሚነት ከላይ ለተጠቀሱ ሁለት ኣላማዎች ሲባል መፈፀሙ መደምደም ይቻላል"
መምህር Nebiyu Sihul Mikael