Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Zreal
Member
Posts: 486
Joined: 15 Mar 2019, 20:33

ሴራና ብርሀኑ ነጋ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታወች!

Post by Zreal » 16 Dec 2019, 06:46

ሴራና ብርሀኑ ነጋ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታወች!

ድሮ ድሮ እንግሊዝና ፈረንሳይ የመቶ አመት ጦርነት አካሒደዋል የሚል ታሪክ ስሰማ የጊዜው መርዘም ያስገርመኝ ጀመር። አሁን አሁን ግን 70 ዓመት ሙሉ እድሚያቸውን በሴራ ያሳለፉ ሰዎች ስለ መኖራቸው ስሰማ የቀደመው ግርምቴ ሊለቀኝ ችሏል። ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አምስት ፓርቲዎች ላይ ስለ መሳተፉ እነዚህን ፓርቲዎች በማፍረስም የአንበሳውን ድርሻ እንደ ሚወስድ መላ ኢትዮጵያ የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ኢህአፓ ፣
ቀስተ ደመና ፣
ቅንጅት ፣
ግንቦት ሰባት ፣
ኢዜማ( ያልፈረሰ)

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ሰሞኑን በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንግድ ሆኖ ቀርቦ ነበር። እናም እንደ ለመደው ብዙ ውሸቶችን ሲቀድ ሰማሁት ከነዚህም ውስጥ።

፨ ቀስተ ደመና ሲመሰረት ወደ ፖለቲካ የገባሁት በሰዎች ግፊት ነው። ይኸ ማለት ቅንጅት ላይም የተሳተፍኩት በሰዎች ግፊት እንጅ በፍላጎቴ አደለም ማለቱ ነው። እውነቱን የሚያውቁ ጎዶቹ ግን ከመሳተፍ ፍላጎትም አልፎ ዝናየን ልደቱ አያሌው ነጠቀኝ በማለት ልደቱ አያሌውን ለማጥፋት ሲተጋ እንደነበር ነው።

፨ ኢህአዴግ በግለሰቦች በኩል ስልጣን እንስጥህ ብሎኝ ነበር ነገር ግን በሪዮት ስለማንገናኝ አልፈልግም ብያለሁ። ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን በውስጥ በአማካሪነት እንደሰራ ነው። ሲጀመር ፕሮፌሰሩ የሪዮት ሎያሊቲ ሳይሆን የስልጣን ፍቅር ነው የሚያስጨንቀው ኢህዴግ የሚያራምደው(በጫካ) የአልቤንያን ኮሚኒዝም ነው ብሏል። ኢህአፓም ከዚህ የተለየ አቋም አልነበረውም።

፨ እስር ቤት በገባሁበት ወቅት 80%ቱ እስረኛ ኦሮሞ ነው። ይኸ ንግግሩ ለአማራው ያለውን ጥላቻ ነው እንጅ በ97ዓም ምርጫ ኢህአዴግ ጥርሱን የነከሰው በአዲስ አበባ ፣ በአማራና በጉራጌ እንደነበር ኢህአዴግ ውስጥ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትሩፋት ባለ ቤት አልባ ከተማ በሚለው መጽሐፉ ገልጿል። ከዚህም በተረፈ ባለፉት 27 ዓመታት እስር ቤቱን ሲያጨናንቅ ፣ ሲኮላሽ ፣ ጥፍሩን ሲነቀል ፣ ተዘቅዝቆ ሲገረፍ ፣ በተመሳሳይ ጾታ ሲደፈር ፣ አጸያፊ ስድብ ሲሰደብ የኖረው አማራ ስለ መሆኑ ታሪክ መዝግቦታል።



Asanodik166
Member
Posts: 9
Joined: 03 Dec 2019, 07:43

Re: ሴራና ብርሀኑ ነጋ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታወች!

Post by Asanodik166 » 16 Dec 2019, 09:30

It's very funny why tplf is so affraid of birhau. He is simply a trustworthy politician.

Post Reply