ጌታቸው ረዳ የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የቦርድ አባል ነው። እንግዲህ የቦርድ አባል የሆነበትን ተቋም ነው "የሽብር መሳሪያ" ብሎ የሚከሰው። ጌታቸው ረዳ ታዲያ ተቋሙ እሱ በሚለው መልኩ ከሆነ እሱ ራሱ ተጠያቂ መሆኑን ማን ይንገረው? የቦርድ አባልነት ቱባ ኃላፊነት ስልጣን ይዞ ለማስተካከል ምን አደረገ?
-
ተቋሙ የሽብር መሳሪያ ከሆነ ጌታቸውን ጨምሮ አመራሩ አሸባሪ ነው ማለት ነው? በእርግጥ ጌታቸውን አሸባሪወች በሆዱ የገዙት ተላላኪ ነው። ለማንኛውም ዋልታ ላይ የሆነውን ነገር ራሱ ጌታቸው ረዳ ነው ትዕዛዝ ሰጥቶ ያስደረገው፤ ይህን ደግሞ በቅርቡ እናረጋግጣለን። ከሌሎች ተቋማት ይልቅ ዋልታ ለምን ተመረጠ?
-
1) ጌታቸው ረዳ የቦርድ አባል ስለሆነ ይኼ ኃላፊነቱ ከመስሪያ ቤቱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖረው በማስቻሉና ያለውን ኃላፊነትና ትስስር በመጠቀም የህወሓት አባላት የሆኑ የመስሪያ ቤቱ ሰወችን ለማዘዝ ችሏል
.
2) ዋልታ እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት የህወሓት ዋነኛ የፕሮፖጋንዳ ማሽን የነበረ ተቋም ነው። ከለውጡ በኋላ መስሪያ ቤቱን ወደ ተሻለ አሰራርና ባህል ለመለወጥ ዋና ኃላፊን ከመቀየር ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። ይሁንና ለውጦችም ተደርገው የህወሓትን አፍራሽ አስተሳሰብ የተሸከሙ አባላቶች አሁንም ስላሉ በእነሱ በኩል ሴራ ለመስራት ተችሏል። እነዚህ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ የህወሓት ሰወች ከካሜራ ማን ጀምሮ እስከ ጋዜጠኛ ህወሓትን የሚቃወሙ ተጋሩ ለቃለመጠይቅ ሲሄዱ የሚያንቋሽሹ፣ የሚሳደቡና የሚያንጓጥጡ ናቸው። እንዲህ ዓይነቱን ተግባራቸውን የትናንትናው ድርጊት ከመፈጸሙ ሳምንት በፊት የአረናው ሚኪ ተስፋይ ሚኪ ተስፋይ አጋልጦ ነበር።
.
3) ዋልታ ትኩረት የተደረገበት ሌላኛው ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህወሓትን የሚያጋልጡ ብዙ ወንጀሎችንና የ27 ዓመት የድርጅቱን ሸፍጥና ብልግና እንዲሁም ንቅዘት የሚያሳዩ ዝግጅቶችን እየሰራ ስለሚገኝ ነው። ህወሓት በዋልታ ፕሮግራሞች በጣም ስለተሸበሩ የእነሱ ወንጀል ለመሸፈን እና ሴራና ብልግናቸው እንዳይነገር ተቋሙን በህግ ለመጠየቅ ከዚህ በፊት ሞክረው የማያዋጣቸው ሆኖ ትተውት ነበር። ምናልባት የትናንትናው ሴራቸውን ለህግ ግብአት ይጠቀሙበት ይሆናል።
.
እንግዲህ ህወሓት የራስ ምታት የሆነበትን ተቋም ለማዳከም የራሱን የድርጅቱን ሰወች በመጠቀም ነው ይኼን ሁሉ ያደረገው። መስሪያ ቤቱ በእንዲህ ዓይነት ነውረኛ ተግባር የተሳተፈውን ሰራተኛ እርምጃ ቢወስድበት ደግሞ "ትግራዋይ ስለሆነ በማንነቱ ተባረረ" ብለው ለቅሶውን ያቀልጡታል። እነ ከበቡሽም ሰው በማንነቱ መጠቃት የለበትም ብለው ሀዘን ይደርሷቸዋል አብረው ያላቅሷቸዋል። በዋልታ ጉዳይ ላይ ከበቡሽና ህወሓት ያሳዩት ጥምረት አፍላ ፍቅረኞችን የሚያስንቅ ነው።
-
ለማንኛውም አስቀድማችሁ ተዘጋጁ
----------
ዋልታ ላይ የተሰራው ዓይነት ተግባር ወደፊት በሌሎች የመንግስት ተቋማትም እንደሚኖር ከወዲሁ መረጃወች ያሳያሉ። በማንኛውም ቦታ የሚሰሩ የህወሓት አባላት የመንግስትን ስም የሚያጎድፍ፣ የተቋማትን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት፣ አሁን አገር እያስተዳደረ ያለው አካል በአሉታዊነት እንዲታይ የሚያደርጉ ስራወችን በተመደቡበት ቦታ ሁሉ በያሉበት እንዲፈጽሙ ተልዕኮ ተሰጥቷቹዋል።
.
በተለይ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚገኙ የህወሓት አባላት ይህን ተግባር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች እና ተግባራት እንዲፈጽሙት ከህወሓት ማዕከላዊ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። በማህበራዊ ገጾች የምናስተውላቸውን የህወሓት ሰወች ጥላቻና አፍራሽ አመለካከቶች መሬት ላይ ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ ከተጠኑ በኋላ ለፈጻሚወቹ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
-
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42