Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 36895
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኢዜማ እና ብልጽግና ፓርቲዎች መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Post by Horus » 14 Dec 2019, 23:12

ለግዜው የሁለቱን ፓርቲዎች ሙሉ ፕሮግራሞችን ትተን በትላልቅ ጽንሶች ላይ ያሉ ነገሮችን እንጠይቅ?

ሁለቱ የፕለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሲስተም የሚቀርጹ፣ የሚያደራጁ፣ የሚያዋቅሩ፣ የሚመሩ ስለሚሆን የፖለቲካ ሲስተም ሞዴላቸው ምንድን ነው? መደመርም ሆነ ብልጽኛ ኢትዮጵያ ወደ ፊት የሚኖራት የፕለቲካ ስርአት ወይም ሲስተም ሞደል ምን ይመስላል?

ይህ ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።

መደመር አንድ እስትራተጂ ነው እንጂ ሙሉ የሲስተም ሞደል ወይም ቲኦሪ አይደለም ። ከዚህ ቀደም እንዳልኩት ብልጽግና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሲስተም ብሎም ኢኮኖሚ ሲስተም ላይ ያለው ፍልስፍና፣ ቲኦሪ፣ ሜትዶሎጂ ወይም እስትራተጂ (መደመር ነው) እና ትግበራው በግልጽ ማሳወቅ አለበት ።

ይህ ለኢዜማን ይሰራል ። ግን ኢዜማ እንደ ሶሺያል ዴሞክራሲ ፓርቲ ባብዛኛው ፍልስፍናው፣ ቲኦሪው ይታወቃል ። ግን እስትራተጂውና ትግበራው በተልይ ሕግ መንግስት፣ የመንግስት አውቃቀር፣ ፈደራል አወቃቅር ላይ ሁልቱ በግልጽ መውጣት አለባቸው ።

ብልጽግኛ የሲስተሙ መጨረሻ መሰረት ግለስብና ብሄር ሲል ኢዜማ ዜጋ ነው ይላል ። እነዚህ ግዙፍ ልዩነቶች ናቸው ።

አንድ ሶሺያል ሲስተም የሚቆምበት መሰረታዊ ፕሪንሲፕልስ፣ የሚፈይዳቸው ቁልፍ ፋንክሽንስ እና ማከንወኛ ፕሮሴሲስ አሉት

በኢትዮጵያ እነዚህ ይታወቃሉን?

Horus
Senior Member+
Posts: 36895
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢዜማ እና ብልጽግና ፓርቲዎች መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Post by Horus » 14 Dec 2019, 23:54

በመሰረቱ ለመጀመር ያህል ብዙ መልካም ነገሮች ይታያሉ ፤ ለምሳሌ ከሲስተም ፕሪንሲፕል ወይም መሰረቶች እንጀምር ።

አንደኛ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሲስተም ክፍት የሆነ፣ ሁሉም ባለድርሻዎች የሚካተቱበት አሳታፊ ማለትም እነዚህ ባለድርሻዎች እስቴክ ሆልደርስ ተስማምተው፣ ተቀናጅተው፣ ተደራድረው፣ ተለያይተው በየግዜው እያረሙ፣ እያስተካከሉ፣ የሚያዘምኑት ሲስተም ነው መባሉ ትልቅ ነገር ነው ።

ንጋት የተሰኘው ስብስብ ይህን እያረገ ነው ። ግሩም ስራ ነው በትክክል እና በእውቀት ከተሰራ፣ ትልቅ የሲስተም ቲኦሪ ዘዴ ስለሆነ ።

ሁለት ፣ ሲስተም መድረሻ ፐርፐዝ አለው ። ይህ እኔ የኢትዮጵያ አጀንዳ የምለው ነው ። በሱ ላይ ኢዜማ ግልጽ ነው ። ብልጽግና ሙሉ አይደለም ። ሆኖም የዛሬ የደንድአ ቃለ መጠይቅ በይበልጥ የተብራራ ነው። (የኢትዮጵያ አጀንዳ፤ (1) የኢትዮጵያ አንድነት፣ መረጋታና ጥንካሬ፤ (2) ዴሞክራሲ፣ ነጻነትና ፍትህ፤ (3) ብልጽግና፣ ትምህርትና ጤና፤ (4) የሚፈጠር፣ ከባቢ ሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ካልቸር)

ሶስት አንድ ሶሺያል ሲስተም ራሱ ሙሉ ተቋም ሆኖ በውስጡ እጅግ ብዙ ክፍሎች፣ አካላት አሉት ። እነዚህ አካላት ግለሰቦች፣ ፓርቲዎች፣ ጎሳዎች፣ ጾታዎች፣ መደቦች፣ የሲቪል ማህበሮች፣ የሙያ ድርጅቶች ወዘተ እንዴ ኢንተራክት እንደ ሚያረጉ ክፍልና ሙሉ አካል እንዴት እንደ ሚሆኑ አልተሰራም።

በዚህ ምክን ያት ነው ተማርን የሚሉ እነ ጃዋር ሲስተም እንዴት እንደ ሚፈጠር ሳይማሩ እስትራተጂስት ተብለው 100 ሚሊዮን ሕዝብ ሚያምሱት ። ባለ ብዙ አካላት ሲስተም መፍጠር ይቻላል፤ እሱም የሲስተምስ ሞዴል ነው። ይህን ሰምታችሁ ታቃላችሁ?

አራት ፣ ያንድ ሲስተም ባለድርሻዎች አብረው ሲሰሩም ሆነ ሲጋጩ የሚከተል ውጤት አለ፤ ይህን በተመለከተ ፓርቲዎች የሚሉት ብዙ ነገር የለም ። እንደ ሲስተም ቲኦሪ ከሆነ፣ በሶሺያል ስርአት ሁኔታ የደፊቱን መተንበይ አንችልም ግን ወደ ፊት ሊፈጠር ከሚችሉት ሰናሪዮች መርጠን የምንወደውን መምረጥ እንችላለን ።

ንጋት ይህን ሊያረግ እየሞከረ ነው

ግን ስንት ሰው ይህን ያቃል?

አምስት፣ በመጨረሻም ትልቁ ዝሆን ሲስተም ዳይናሚክስ ይባላል።

እኔ ብዙ ግዜ የካራምቦላ ጠረጴዛ የምለው ነው። በሲስተሙ ውስጥ ካሉት ተጫዋቾች አንዱ አንድ እርምጃ ሲወስድ ሁሉም ይነቃነቃሉ ፣ የሁሉም ቦታቸው ፣ ታክቲካቸው ይለወጣል ፣ ጨዋታው ይለወጣል ።

በኔ ግምት ጃዋርና ዎያኔ ይህን ፕሪንሲፕል የሰሙት አይመስለኝም ። አንድ እርምጃ ስንወስድ የሚነቃነቁትን ጠጠሮች በውል ካላወቅን የፖለቲካ ተጫዋች መባል አንችልም ።

Halafi Mengedi
Senior Member+
Posts: 47266
Joined: 30 May 2010, 23:04

Re: በኢዜማ እና ብልጽግና ፓርቲዎች መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Post by Halafi Mengedi » 15 Dec 2019, 01:36

Good question and the difference is strikingly different as depicted below:



Horus
Senior Member+
Posts: 36895
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢዜማ እና ብልጽግና ፓርቲዎች መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Post by Horus » 15 Dec 2019, 01:48

በኢዜማና በብልጽድና ፓርቲዎች መሃል የሃሳብ መገናኘት፣ መመሳሰል ቢኖር እሰዬ ነው። እንደ እኔ እንደ እኔ ኢዜማና ብልጽግና አንድ ሆነው ወይም ግንባር ቢፈጥሩ ላገራችህን ትልቅ ትቅም ነው። አንድ መኪና ባንድ ግዜ በ4 አቅጣጫ አይሄድም። ደሞ እነዚህ ፓርቲዎች ልብ ካገኙ አንድ ሆነው ኢትዮጵያን በፍጥነት አንድ ማድረግ ይችላሉ።

Horus
Senior Member+
Posts: 36895
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢዜማ እና ብልጽግና ፓርቲዎች መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

Post by Horus » 15 Dec 2019, 03:15

TembienLiberation wrote:
15 Dec 2019, 02:31
ኢዜማ = EPP = Ethiopian = Ethiopia's renaisance!
ተምቤን ሊበሬሽ፤
ባብዛኛው ትክክል ነህ ፤ ግን ዜጋና ብሄር እንዴት ይዋሃዱ የሚለው ላይ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ ያማራ ዘረኞችን ደስ የማያሰኝ ነገር ስላለ ችግሩ ሙሉ በሙሉ አልተፈታም ። ዞሮ ዞሮ ግ ን ኢትዮጵያ ባሸናፊነት እንደ ምትወጣ ጥርጥር የለኝም !!


Post Reply