ሲነርጂ ወይም አብሮ መስራት ከሚለው ውጭ ለመደመር መስጠት ወደ ስህተት ይወስዳል።
ለምሳሌ ኢትዮጵያ የብሄሮች ወይም ጎሳዎች ድምር አይደለችም። ኢትዮጵያ አንድ ሙሉ ማህበራዊ ሲስተም ወይም ስርአት ነው።
ለምሳሌ ዜጋዎችና ጎሳዎች ያዋሃደ የኢትዮጵያ ማህበራዊ ሲስተም ወይም ፌዴሬሽን የግለሰቦችና ጎሳዎች ድምር ሲስተም አይደለም ። የኢትዮጵያ ሰርአት ስንል አንድ ራሱን የቻለ ሙሉ ሰር አት ማለት ነው።
አንድ ሲስተም ሲስተም የሚያሰኘው ትልቁና ብቸኛው ነገር አብሮ መስራት ወይም ሲነርጂ የሚለው ጽንስ ነው። ያንድ ሲስተም አካልት ክፍሎች አብረው ካልሰሩ ሺ ጊዜ ቢዋቀር ቢተሳሰር ቢደመር ሲስተም አይሆንም ።
ለዚህ ነው መደመር ሲባል ሁሉን ነገር ትተን ስለ አብሮ መስራት ነው ማሰብ ያለብን።
ለምሳሌ ጎሳዎች በዙ አልበዙ፣ ክልሎች ኖሩ አልኖሩ ፣ ፓርቲዎች ተዋሃዱ አልተዋሃዱ ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያ አንድ ሲስተም ስለሆነች እነዚህ ሁሉ አብረው ካልሰሩ አንዳቸውም ሊያድጉ ወይም ግባቸው ሊደርሱ አይችሉም።
መደመር ዝም ብለን አብሮ መስራት ብንለው በጣም ቀጥ ያለ ቀላል ጽንሰ ሃሳብ ይሆናል ።