Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

በምስረታ ላይ ከሚገኘው አማራ ባንክ አ/ማ የተሰጠ መግለጫ

Post by Maxi » 10 Dec 2019, 12:57



በምስረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አ/ማ የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜ መራዘሙን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ASRAT MEDIA HOUSE

በምስረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አ/ማ የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜ መራዘሙን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

(ኅዳር 30 ቀን 2012 ዓ/ም)

አማራ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 592/2008 ዓ/ም እና ከባንክ ምስረታ ጋር የተያያዙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣቸው መመርያዎች እና ደንቦችን በመከተል በመመስረት ላይ ያለ የሕዝብ ባንክ ነው። የአማራ ባንክ አ/ማ በሀገራችን ልማት ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት፣ የባንክ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የበለጠ የማዳረስ እቅድን ታሳቢ ያደረገ ቢዝነስ ሞዴል በመከተል የባንክ ስራ ለመጀመር እየተዘጋጀ እና የምስረታ ሂደትን እያከናወነ ያለ ባንክ ነው።

በዚህም መሰረት አደራጅ ኮሚቴ አቋቁሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ደንብ በሚያዘው መሰረት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ለሕዝብ አክሲዮን መሸጥ የሚያስችለውን ውሳኔ አግኝቷል። ከነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮም የመስራቾች አክሲዮን እየሸጠ ይገኛል።

አክሲዮን ሽያጩ በሀገራችን ሰፊ ተደራሽነት ባላቸው አስር ባንኮች እየተካሄደና ህብረተሰቡም እየገዛ ይገኛል። የሽያጩ ሂደቱን የሚያስተባብር ቢሮም በአዲስ አበባ ከተማ ካሳንችስ አካባቢ ቢሮ ከፍቶ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ ነው። በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አ/ማ እስከ ኅዳር 30/2012 ዓ/ም ድረስ ባደረገው ሽያጭ የተከፈለ አክሲዮን ብር 1 ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሶስት (1,632,000,403)፣ቃል የተገባ ብር 2 ቢሊዮን አንድ መቶ ሀያ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ሽህ ስድስት መቶ አርባ (2,128,690,640) ሲሆን እስከተጠቀሰው ጊዜ ድረስ ቁጥራቸው 31 ሺህ በላይ የሆኑ መስራች አክሲዮን አባላት ተመዝግበዋል።

ባንኩ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የአክሲዮን ሽያጩን እያከናወነ ቆይቶ ሽያጩን የሚያጠናቅቅበት ጊዜ ኅዳር 30/2012 ዓ/ም መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። ነገር ግን ከተለያዩ የህብረተሰብ አካላት በርካታ የማራዘሚያ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ለምሳሌ ያህል ከሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ጋር በተያያዘ አርሶአደሮች አክሲዮን ለመግዛት ጊዜው እንዳነሰባቸው በመጠየቃቸው እና የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፋይናንስ ሴክተሩ የአክሲዮን ባለቤት መሆን የሚያስችላቸው አዲስ አዋጅ የፀደቀ መሆኑን ተከትሎ የአክሲዮን ግዢ ጥያቄያዎችን አቅርበዋል። በእነዚህ ልዩ ልዩ ምክንያቶች የጊዜ መጣበብ ያጋጠማቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለማስተናገድ ጊዜ መስጠት ተገቢ መሆኑን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ አምኖበታል።

ስለዚህ በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አ/ማ የመስራቾች የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ እያስታወቀ በዚህ አጋጣሚ የባንኩ መስራች ባለ አክሲዮን ለመሆን ወስናችሁ የአክሲዮ ሽያጭ ማራዘሚያ ጊዜውን በመጠቀም ለመግዛት ለምትጠባበቁ እንዲሁም ለስራችን መቃናት ትብብር ላደረጋችሁ አደራጅ ኮሚቴው ምስጋናውን ያቀርባል።

(አሥራት፣ አማራ ባንክ በሸራተን ሆቴል ባደረገው መግለጫ ተገኝቶ ማረጋገጥ እንደቻለው ከላይ በመግለጫው ዝርዝር ከተጠቀሰው በተጨማሪ መግለጫ በሚሰጥበት ወቅትም ሽያጩ ከፍ እንዳለና የተከፈለው የአክሲዮን ሽያጭ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን እንዲሁም ቃል የተገባው ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ አድጓል።)

@@
Member
Posts: 1498
Joined: 05 Dec 2014, 11:35

Re: በምስረታ ላይ ከሚገኘው አማራ ባንክ አ/ማ የተሰጠ መግለጫ

Post by @@ » 10 Dec 2019, 13:14

the video is from 2 weeks ago. many investors and money added in just two weeks.


Post Reply