የሟቹ ኢሕአዴግ ፖለቲካ "ብሔሮችን" በተመለከተ ዋነኛ አረዳዱ ለሥልጣን መወጣጫነት መጠቀሚያ እርካብ (instrumentalist) አድርጎ ያያቸዋል ቋንቋን ብቸኛ የማንነት መበየኛ አድርጎ የሚያየው ኃይል "ከታሪካችን የወረሰነውን የተዛባ የሕዝብ ግንኙነት በማረም የጋራ ጥቅማችንን" እናሳድጋለን ብሎ በሕገመንግሥቱ ቢደነግግም ÷ ሥርዓቱ የአዳዲስ የፖለቲካ ቅራኔዎች ምንጭ ሆኖ ታይቷል።
ቀድንሞውን ያልነበረ ቋንቋ ተናጋሪነትን መነሻ ያደረገ የገቢ -ኢ-እኩልነት የታየው ድኀረ ደርግ ስለመሆኑ መካድ አይቻልም የብሔር ማንነት" የልሂቃኑ የሥልጣን መወጣጫ እርካብ ሆኖ ቢቀርብም ÷ ደረጃ መዳቢው የሥርዓቱ መሃንዲስ የነበሩት የህወሃት ጥቂት ሰዎች ነበሩ ። የአስኳሉን ስብስብ [core group] የአድዋ ገዥ መደብ ልንለው እንችላለን። ያም ሆኖ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ዝምድናን ታሳቢ ያደረጉ ሥርዓታዊ ጥቅሞች በተዋረድ የዘነበላቸው ነበሩ ። የባንክ ብድር ይሁን የኮንትሮባንድ ንግድ አረንጓዴ መብራቶች ምንጫቸው የሟቹን ኢሕአዴግ የበላይነት ጨብጦ የኖረው ኀይል ነበሩ።
በዚህ ሁሉ መዋቅራዊ ምዝበራ "የብሔር ብሔረሰቦች ቀን" በሚል መከበር መጀመሩ ደግሞ መፀቱን አብዝቶት ታይቷል። 1998 የጀመረው ይሄ "በዓል" "ብሔሮች" ባላችሁበት እርገጡ የሚል አንድምታ ነበረው ። በበዓሉ ቀን በአናታቸው ላይ ቀንድ የሰኩ primitive societies እና የፊት ገፅታቸው በወርቅ የተሸፈኑ የአንድ ብሔር ተወላጆች እኩል በአንድ መድረክ እንዲታዮ ይደረግ ነበር ።
ደቡብ ኦማ ውስጥ በቅድመ ምኒልክ ማንነታቸው ይኖሩ የነበሩ አስራ ስድስት የሚደርሱ የማንነት ቡድኖች ድኀረ ደርግ ራቁታቸውን መኖራቸው ሕገመንግሥታዊ የመብት ጥበቃ የሚደረግለት "የብሔሮች መብት" ተደርጎ ተቆጥሮላቸዋል። የነገሩ ምፀት አፄ ምኒልክን እየረገሙ የድኀረ-ደርጉን የቋንቋ ነጋዴ ራቁታቸውን ቁመው እንዲያመሰግኑ መደረጉ ነው ።
ከ1998 ጀምሮ በአንድ መድረክ ደረጃ ተሰባስበው ይሄን እንዲያደርጉ ሕዳር 29 ተመርጦ ላለፉት አስራ አራት ዓመታት በአደባባይ ታይቷል። ያን-ጊዜ እንዳሻው የፏለለበት ኀይል በታሪክ ፊት ተሸናፊ ቢሆንም ÷ ያነበረው ሥርዓት ውርሶቹ (legacies)ለ'ተረኛ ነን' ባዮ ቡድን የተመቹ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።
የዘንድሮው ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› ሲከበር
የሚከተሉት ነገሮች እንዳይዘነጉ !
ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ዜግነት ተቀብሮ ዘውጌ ብሄርተኝነት ወደ አገራዊ ህልውና አናጊነት ማደጉን÷
ሰዎች በዘራቸው ተለይተው ከሚኖሩበት ቀየ መፈናቀላቸውን፤
በሁሉም ክልሎች እና ጎረቤት አገራት ‹‹ተከበረው እና ተፈርተው›› ይኖሩ የነበሩ ህወሃት "ምርጥ" ይላቸው የነበሩ ዜጎቹ ብቻ እንደነበሩ፤
ለም መሬት በቅንጣቢ ሳንቲም እየቸበቸቡ የከተማውን ደሃ እና የገጠሩን አርሶ አደር ማፈናቀል የሃያ ሰባት ዓመት ፖለቲካዊ ቸነፈር እንደነበር፤
የሰባ ዓመት አዛውንት ‹‹ከክልላችን ውጣ›› በሚል ኃይል መጠቀም የከፋ የፖለቲካ ጣኔ መሆኑን በተግባር ያየንበት ስለመሆኑ፤
"የፖርቲ አባል ካልሆንክ ሥራ አታገኝም" በማለት
ጠባሳው የማይሽር የፖለቲካ ችጋር በተቋማት ደረጃ እንደታየ፤
ለምን የተቃውሞ ድምጽ አሰማችሁ?' በሚል ወህኒ ተወርውረው የተኮላሹ፣ የተደፈሩ፣ የተሰቃዩ ብሎም በግለጽና በስውር የተረሸኑ ወገኖች እንዳሉ አንዘንጋ፡፡
ራሱን ‹‹መንግሥት ነኝ›› የሚል አካል ከግለሰብ ጋር ብሽሽቅ ውስጥ ገብቶ እንደታየ፣
ከሰፈር ጎረምሳ ለይተን የማናየውና በቀልተኝነት መለያው የሆነ ዘረኛ ቡድን የፖለቲካ ድህነት መገለጫው ሆኖ እንደኖረ አንዘንጋው፡፡
ለወሊድ የደረሱ ሴቶች በአማራነታቸው ተመርጠው እንዲመክኑ እንደተደረገ ፍጽም አንዘነጋውም ።
ይሄ ድርጊት ስታሊን በራሻ፣ ሂትለር በጀርመን በአይሁዶች ላይ አልፈፀሙትም:: ሃፊዝ አልአሳድም ሆነ በሽር አልአሳድ በሱኒ ሙስሊሞች ላይ በሶሪያ ያልፈጸሙት ልዩ ወንጀል ነው። በየትም ሀገር ያልታየ ይቅርታ ለማድረግ የሚከብድ የሃያ ሰባት ዓመት ፖለቲካዊ ወንጀል ነው፡፡ ገና በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ መሆኑ አይዘንጋ ።
እንዲህ ያለ የነጠፈ ህሊና የሚነዳው ክቡድ ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (ICC) ካልሆነ በየትኛው ችሎት ይታያል?
አትርሱ
በግብር ስም ከድሃ ጉሮሮ በመጠንቅ በተዘረፈ ሃብት፤ የሲሚንቶ ቁልል ተራራ መስራት በአፓርታማ መንበሽበሽ ፣ ዘመናዊ ተሸከርካሪ መዘወር፣በጥጋብ ስሜት ድሆችን መርገጥ፣ ለዝሙት ተግባር ዱባይና ሩቅምስራቅ አገራት ድረስ ቪያግራ ተሸክሞ መዝመት…የሃያ ሰባት ዓመቱ
ውላጅ የፖለቲካ በሽታዎች ናቸው፡፡
ከወገን ይልቅ ባእድ የሚያስቀድም የአገር ገዢ የፖለቲካ
ችጋር ያጠናገረው እንጅ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? እነዚህ ህሊናቸው የሞተባቸውና ቂም ቀብትቶ የያዛቸው ህወሓታውያን እና የቀድሞ ሥርዓቱ የአንቀልባ ልጆች ÷ ደሙን ሲመጡት የኖሩት ምስኪን ህዝብ በ"ብሔር ብሔረሰቦች መብት" ስም ሲነግዱበት ኑረዋል፡፡
ስንቱን ልሂቅ ነኝ ባይ የፖለቲካ ችጋር እንደመታው በአዳባባይ ሲያጋልጡት አየን? "ብሔር ብሔረሰቦችስ" ለጥቅመኛ ልሂቃን መናጆ አልሆኑም?
የሆነብንን ሁሉ አንዘንጋ!
ያለፈው ሃያ ሰባት ዓመት የህወሃት ጸረ-ሕዝብ ዘመቻ የፖለቲካ ቸነፈር ሆኖብን ስንቱን ዘረረ?
የስንቱን ደጅ ዘጋ?
ስንቱን እንደ ወጣ አስቀረ?
እነዚህንና መሰል ጉዳዮች እያሰብን፤ ያለፈው ሃያ ሰባት ዓመት የፖለቲካል-ኢኮኖሚ መዋቅር ለነማን ዘነበ? ለነማንስ አካፋ? ለየትኞቹስ መከራን አወረደ? ...
የሚለውን በጥልቅ እየመረመርን ቅድመ-ምኒልክም ሆነ ድኀረ ምኒልክ የኖሩትን ÷ ወደፊትም የሚኖሩትን "ብሔር ብሔረሰቦች" በመድረክ ላይ ሲጨፍሩ ዛሬ እያየን ነው፡፡ መድረኩ ብቻ ሳይሆን የ"በዓሉ" አንድምታ ከትላንቱ ለመለየቱም እንፈትሻለን ።
ካለሕዝባዊ ተሳትፎ በፀደቀው ሕገ-መንግሥት ውስጥ በመግቢያው ላይ "ከታሪካችን የወረስነው የተዛባ የሕዝብ ግንኙነት'' እንዳለ ያመለክታል ። ለኔ ከቅድመ 1983 ይልቅ ባለፈው ሃያ ሰባት ዓመት በ"ሕዝቦች" መካከል የተዛባ ግንኙነትም ሆነ የዕድገት ልዮነት ታይቷል ።
ማሳያ ካስፈለገ ከስር ያለውን ፎቶ ይመልከቱ ። ቢያንስ አንደኛው ወገን ከቅድመ 1983ቱ ይዞታ በእጅጉ ተለይቷል ። በእጅጉ! ከዚህ በላይ የተዛባ የ"ሕዝቦች ግንኙነት" ሆነ የዕድገት ልዮነት ማሳያ ይኖር ይሆን ?
የዛሬው "የብሔር ብሔረሰቦች ቀን" እንደ ቀዳሚዎቹ ሁሉ ÷ ተረኛ ነን ባይ ለሆኑ ኦነጋውያን መጠቀሚያ እንዳይሆን በር በሩን ዝጋ! ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች የፖሊሲ ጥበቃ ማድረግና በቋንቋ መነገድ ይለያያሉ። የእስከዛሬው የቋንቋ ማንነት ነጋዴዎች የነገሱበት ጥቂት ጥቅመኞች የሥልጣንና የሃብት ምንጭ ያደረጉት "ቀን" ነበር "በዓል" ተብሎ ሲከበር የነበረው ። እኛ ይቅር የምንለው ንግዱን እንጁ ብዝሃ ቋንቋውን አልያም ባህሉን አይደለም።
በብዝሃ ባህል የደመቀች አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
[ከስር ያሉ ፎቶዎች 'ቦዲ' ÷ 'ትግሬ'÷ 'አማራ' ይወክላሉ። ይሄ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ገፅታ ነው]
ፎቶዎቹ የተሸከሙት እውነት መቼም የትም እንዳይደገሙ!
ሙሉአለም ገ.


