እኔ ሆረስ እባላለሁ፣ ቃላት መሰንጠቅ አይመቸኝም፤ እና ባጭሩ እነሆ ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር መፍትሄ ያጣው ለችግሩ ትክክለኛ ስም ሰጥተን እና ችግሩ ምን እንደሆነ ማወቅ ስላልቻልን ነው ።
የኢትዮጵያ ችግር የማንነት አለመኖር፣ የማንነት አለመታወቅ ወይም የማንነት መቀበል፣ አለመከበር አይደለም ። ይህን በውል ያልገባው ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ ግንዛቤ መያዝ አይችልም። ስለዚህ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ 'ማንነታችን ይከበር' የሚሉ ሁሉ ጊዜና ጉልበታቸውን በከንቱ ነው የሚያባክኑት ።
ማንነት ያንድ ነገር ምልክት፣ ያንድ ነገር ስም፣ ያንድ ነገር መታወቂያ፣ መለያ መልኩ፣ ቅርጹ ወይም መጠሪያ ነው ። በቃ ! ባሁን ግዜ አንድ ሰው ዶጮ ነኝ፣ ሌላው ኮቦ ነኝ፣ ሌላው ጾቤ ነኝ ቢል አንድም ተቃዋሚ የለውም ። በቃ !
በኢትዮጵጵያ ያለው የምንነት ጥያቄ ነው ። በእንግሊዝ ቋንቋ ዲግኒቲ ማለትም ያንድ ሰው ዋጋ፣ ያንድ ሰው ፋዪዳ፣ ያንድ ሰው ሚዛን ወይም ያንድ ሰው ስኬት ሜሪት ማለት ነው። በእንግሊዝ ሰልፍ ኤስቲም ይባላል። ሰልፍ ኤስቲም ደሞ ከሌላ ሰው የሚገኝ ዋጋ አይደለም ። አንድ ሰው ከራሱ፣ አንድ ሕዝብ ከእምነቱና ባህሉ የሚያሳድገው ምንነት ነው ። ምንነት ያንድ ሰው ዋጋ፣ የመኖሩ ትርጉም፣ የፍላጎቱ የችሎታው የስራው መገለጫ ማለት ነው።
ስለሆነም አንድ ሰው የሰልፍ ኤስቲም ችግር አለው ሲባል የስኬት፣ የእድገት፣ የሞሟላት ችግር አለው ማለት ነው። ምንነት የሙያ፣ የስራ የስኬት መመዘኛ፣ መለኪያ፣ መግለጫ ጽንስ ነው። የምነንት ችግር ያለባቸው ሰዎች የትንሽነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው ። ይህ የሳይኮሎጂ እንጂ የፖለቲካ ችግር አይደለም ።
ባንድ ቃል ኢትዮጵያን እያመሳት ያለው የማንነት ጥያቄ ሳይሆን የምንነት ሳይኮሎጂያዊ ጥያቄ ነው !!