የተያዙት የተጠርጣሪ አሸባሪዎቹ የት ደረሱ? በሙሉአለም ገ.መድህን
Posted: 07 Dec 2019, 09:34
በመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ዋና መምሪያ ÷ ትንተናና ፕሮዳክሽን እገዛ : በፌዴራል ፖሊስ እና በብሔራዊ መረጃና ደኀንነት ጥምረት አንድ ኦፕሬሽን ተካሂዶ ነበር ። ዘመቻው የISS አባላት ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋልን ይመለከታል ። ኦፕሬሽኑ ከተሰራ አንድ መቶ ቀናት አለፉ ። መረጃው ለሕዝብ ይፋ ከሆነ ደግሞ ዛሬ ዘጠና ሰባተኛ ቀኑ ነው ። ጉዳዮ [የምርመራ ሂደቱ] የት እንደደረሰ ብናውቅ መልካም ነው ። እንደዜጋ ብሎም ግብር ከፋይነታችን መሰል የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶችን ማወቅ ባለብን መጠን [ከተገቢነት አኳያ] መንግሥት የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። ለሁሉም በጉዳዮ ላይ የሚሰማኝን ማለት እፈልጋለሁ ።
-
ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አኳያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለሚከፈቱ የሽብር ጥቃቶች ተጋላጭ ሊያደርጋት ይችላል። በተለይም እንደ አልሸባብ እና አይ. ኤስ አይ. ኤስ. ያሉ የሽብር ቡድኖች ዓለም አቀፍ አደጋ በመሆናቸው እነዚህ የሽብር ቡድኖች ወደሀገር ቤት የሚገቡባቸው ቀዳዳዎች እየሰፉ መጥተዋል፡፡ ሁለቱም የሽብር ቡድኖች ዓለም አቀፍ የጅሃዲስት መረብ በመመስረት የመዋጋት እና ጥቃት የማድረስ አቅማቸውን ለማሳደግ ሲጥሩ የነበሩ ከመሆኑ አኳያ በሀገር ቤት በቅራኔ የተሞሉ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ኃይሎችን ለሽብር ዓላማቸው ማስፈጸሚያ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፡፡
-
በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የአክራሪነት ዝንባሌ ለዚህ መሰል የሽብር ዓላማ መጠቀሚያ የመሆን ዕድል አለው፡፡ ይሄ የቅድመ-ንቃት ምልክት የሆነ ታሳቢ ስጋት ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ተሞክሮ ያለው በመሆኑ ስጋቱን ተጨባጭ ያደርገዋል፡፡ለአብነት በኬንያ የአልሸባብ አጋር ሆኖ የተገኘው አል-ሂጅራ የተሰኘው ስብስብ እንደነበር ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡
-
አልሸባብም ሆነ አይ. ኤስ. አይ. ኤሴ. ከጊዜ ወደ ጊዜ እየፈጸሟቸው ያሉ የሽብር ጥቃቶች እና የሚጠቀሟቸው ስልቶች እየተወሳሰቡ መጥተዋል፡፡ በተለይም ‹‹ተክፊር›› እየተባለ የሚጠራው በቀዳሚነት በአልቃይዳ ጥቅም ላይ የዋለውን የትግል ስትራቴጅ ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት ሁለቱ ቡድኖች አደገኝነታቸውን አጉልቶታል፡፡ እንደሽብር ቡድኖቹ የትግል ስትራቴጅ ‹‹ተክፊር›› የእስልምናን አስተምህሮት ከሌሎች ኃይላት ለመጠበቅ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጅሃድ እንቅስቃሴ ለማስፋፋት ሲባል፣ተባባሪ ያልሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ሳይቀር መግደልን እውቅና የሚሰጥ መሆኑ አደጋውን የከፋ አድርጎታል፡፡
-
በውስን የሰው ኃይል፣ በተጠና ታክቲክ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል የሽብር ጥቃት መፈጸም እንደሚቻል፣ በሶማሊያና በኬንያ ያደረሳቸውን ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደተሞክሮ የሚያየው አልሸባብ፣ ከአይ. ኤስ አይ. ኤስ. ጋር በፈጠረው ጥምረት ለቀንዱ ሀገራት ብሔራዊ የደህንነት ስጋት ሆኗል፡፡
-
ኢትዮጵያ ካለችበት ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት አኳያ፣ እነዚህ የሽብር ቡድኖች በፈጠሩት ጥምረት ሀገሪቱን ለሽብር ጥቃት ዒላማ ማድረጋቸው ይጠበቃል፡፡
-
መስከረም /2012 የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የአልሸባብ እና የአይ. ኤስ. አይ. ኤስ. የሽብር ቡድን አባላት በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሰምተን ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት አካላት የምርመራና የፍርድ ሂደት በምን ደረጃ ላይ እንዳለ በይፋ የተሰጠ መግለጫ ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ። ነገሩ በሂደት ላይ ካለም ውሎ አድሮ የምናየው ይሆናል ።
-
በ'ኔ በኩል የሚከተሉት ጥያቄዎች አሉኝ
-
እነዚህ ዓለም ዐቀፍ አሸባሪዎች የኢትዮጵያን መሬት ለመርገጥ የሚያስችል ማኅበራዊ መሠረት እንዴት ሊያገኙ ቻሉ?
የሀገር ውስጥ ወኪሎቻቸው የተባሉ ኢትዮጵያውያን ስለምን ከጸረ-ኢትዮጵያ ኀይሎች ጋር መሰለፍ መረጡ?...
ብሎ መመርመር የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ይኼ አደጋ የዛሬ እና የነገ የኢትዮጵያ ቀዳሚ ብሔራዊ የደህንነት ስጋት ነው፡፡
ከላይ የተመለከትናቸውን ነጥቦች እያሰብን ሽብርተኝነትን ከኢትዮጵያ ብሎም ከአፍሪቃ ቀንድ ማፅዳት ስለምንችልባቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ማሰላሰል የዜግነት ግዴታችን ነው ።

[ማሳሰቢያ:- ይህችን ማስታወሻ ሳሰፍር ራሴን እንደወጣሁበት ብሔር : ሃይማኖት አልያም አገር አይቼ ወይንም ግምት ውስጥ አስገብቼ ሳይሆን ÷ ማስታወሻዋን ስፅፍ ራሴን እንደ አንድ የአፍሪቃ ቀንድ ነዋሪ ቆጥሬ ነው ። በተረፈ አክራሪነት በሁሉም ሃይማኖቶች አለ ። በክርስትናም በአይሁድም... በሌሎችም አለ። ዋናው ነገር ያ -የማክረር ዝንባሌ በአገራዊ ህልውና አደጋ መደቀን አለመደቀኑ ላይ ነው ።
'እኔ ብቻ ፃድቅ ነኝ' ማለት ይቻላል ። 'የእኔን ብቻ ተከተል' ማለት ግን አይቻልም ። የአክራሪነትን ስጋት ስንመለከት ከዚህ አግባብ ሊሆን ይገባል]

ከሽብርተኞች ነፃ የሆነች ዓለም ታስፈልገናለች!
ቅድሚያ ለአገራችንና ለአፍሪቃ ቀንድ!