የጽሁፍዎን እንድምታ ባልጠላውም፤ ላም ከዋለችብት ነውና ዞሮ ዞሮ ከዚያው ራስዎን ከመደቡበት ጎጠኛ ያለመውጣትዎ ግን መርዝዎን እስከልተፉ ድረስ ከአድምታው ጋር ራሴን እንዳላስተያይ ያደርገኛል፡፡ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ናቸው፡፡ ተፍቻለሁ ሲሉ እኔም ለጽሁፍዎ እንድምታ ተግበራዊ ትብብር ለማሳየት ራሴን አስገዛለሁ፡፡
1. “ባለፉት 18 ወራት … ለምሳሌ የአዋሳዉ እልቂት፥ የሻሸመኔዉ ዘቅዝቆ መስቀል፥የቡራዩ ጭፍጨፋ፥ የጌዲኦ መፈናቀል፥ የቤኒሻንጉል ግዲያ፥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች ዉስጥ የሚታየዉ የርስ በርስ ግዲያ እና በቅርቡ የ88 ንጹሃን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈዉ በአንድ ግለሰብ ዙሪያ ያጠነጠነዉ የፖለቲካ ሸፍጥ ዋና ዋናዎቹ ናችዉ።” ብለዋል፡፡ ነገር ግን ስም ማጥፋት ለእናንተ እንደ መመረቅ ነው የሚቆጠረው ካላላቹን በስተቀር በገጃም በድንጋይ ወግሮ መግደል፤ መስግድ ማቃጠልንና በእንጨት ላይ የሚኖር ዝንጀሮ እኮ ነው እያለ የጉምዝን ዘር የሚጨፈጭፈውን ሰይጣን መንፈስ ስለሆነ አላየሁትም ነው የሚሉት?
2. “የምናሳድደዉ ሰዉ ግደል ሲሉት ለምን ሂድ ሲሉት ወዴት ብሎ የማይጠይቅ ጽንፈኛ የሆነ ሃይል አደራጅቷል፥ ጽንፈኛን እኛዉ እራሳችን ጽንፈኛ ሆነን አናሸንፈዉም።” ብለዋል፡፡ ግን ምነው ስለ የእናንተው ጉራኛና ጠብ ጫሪ ባልዲ ራስ ይሁን ወይም ፋኖ አልነገሩን ታዲያ?
ቀኝም ነፈሰ ግራ እውነት ቦታዋን ልትይዝ ጊዜው ግድ ይላል፡፡ ከምክርዎ በፊት እውነት የት አለች፤ መብት ወይስ ጥቅም ይቀድማል የሚለውን በተግባር ለይተው ሲያበቁ በሌላ ጽሁፍዎ ላይ ተንጸባርቆ ባየው ደስ ይለኛል፡፡
በመስቀል ሳም ሰበብ የሀበሻ ጥፍ፤ በምክር አስመስሎ ዘረፋና የብልጣ ብልጥነት ምክር አንቀበልም ነው ያልነው፡፡ በጋራ በሕይዎት ለመኖር መርዝን ተፍቶ ምራቅን መዋጥ ግድ ይላል፡፡
https://www.satenaw.com/amharic/archives/73600