Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Maxi
- Member+
- Posts: 5951
- Joined: 06 Mar 2014, 04:33
Post
by Maxi » 05 Dec 2019, 14:20
ከአማራ ባንክ አክስዮን መግዛት እና የሚያስገኘው ጥቅም!! - እስካሁን ባለአክስዮኖች ከ1,420,000,000.00 (አንድ ቢሊየን አራት መቶ ሚሊየን ብር) ተሰብስቧል!!
የባንክ አክስዮን መግዛት ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው። ሁሉም አማራ ሊገዛ ይገበዋል። ለምሳያሌ ያክል በኢትዮጵያ ያሉ የግል ባንኮች አክስዮን ለገዙ አባላት የሚያስገኙት ትርን በንፅፅር ከዚህ በታች ተመልከቱት። ይህ ትርፍ በአመት ከ1000 ብር የአክስዮን ግዥ የሚገኝ ነው።

Last edited by
Maxi on 05 Dec 2019, 14:29, edited 1 time in total.
-
Maxi
- Member+
- Posts: 5951
- Joined: 06 Mar 2014, 04:33
Post
by Maxi » 05 Dec 2019, 14:26
ክብረ ወሰኑን ከፍ አድርጎ የሰቀለው ባንክ! አማራ ባንክ!
Getachew Shiferaw
December 3 2019
~ የተፈቀደ ካፒታል ብር 2,000,000,000.00 (ሁለት ቢሊየን ብር)፤
~የአክስዮን ሽያጭ የተጀመረው ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም፤
~ እስካሁን የተፈረመ (subscribed) አክስዮን፦ ከብር 1,420,000,000.00 (አንድ ቢሊየን አራት መቶ ሚሊየን ብር) በላይ፤
~ እስካሁን በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ካፒታል (paid up) አክስዮን፦ ከብር 1,114,000,000.00 (አንድ ቢሊየን አንድ መቶ አስራ አራት ሚሊየን ብር) በላይ፤
~ አክስዮኑ አሁንም በሽያጭ ላይ ይገኛል፣ ህዳር 30 ቀን ሽያጩ የሚዘጋበት ቀን ይሆናል።
~ ሽያጩ በይፋ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ አክስዮን ለሚገዙ ባለአክስዮኖች፣ የመስራችነት መብት የተጠበቀ ነው፤ ከዚህ በፊት አክስዮን የገዙ ባለአክስዮኖች ድጋሜ መግዛት ይችላሉ።
~ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች አክስዮን መግዛት የሚችሉት በውጭ ምንዛሬ ብቻ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች በትዕግስት እንድትጠብቁ ተጠይቃችኋል፣ ጥያቄዎቻችሁን እያሰብንበት ነው ተብላችኋል። የብሄራዊ ባንክ መመሪያ እንደወጣ ክፍያ የምትፈጽሙባቸው የውጭ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች እና ማሟላት ያለባችሁ መመዘኛዎች ይለቀቃሉ።
በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አ.ማ አክስዮን ሽያጭ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሸጠ ይገኛል፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ የግል ባንኮች ምስረታ ታሪክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ አክስዮን በመሸጥ፣ የአክስዮን ሽያጭ ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ባንኩን በጠንካራ የካፒታል መሰረት ላይ ለመገንባት በማቀድ የአክስዮን ሽያጩን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በባንክ ስራ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 መሰረት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሙሉ በሙሉ የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያውን ባለቤትነት የተቋቋሙ ኩባንያዎች አክስዮን ለመግዛት የሚችሉ ሲሆን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያውን የውጭ ሀገር ዜጎች አክስዮን መግዛት የሚችሉት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ብቻ ነው። ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች የብሄራዊ ባንክ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ ተብላችኋል፤ የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ስራ ላይ እንደዋለ ክፍያ የምትፈጽሙባቸው የውጭ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች እና ስዊፍት ኮዶቻቸው ይፋ ይደረጋሉ።
በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አ.ማ የአክስዮን ሽያጭ እስከ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ እስከ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ አክስዮን ለሚገዙ የመስራችነት መብት የተጠበቀ ነው።
የባንኩ አደራጆች የባንኩን ምስረታ የሚያበስረውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማከናወን በዝግጅት ላይ ናቸው። ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ የጠቅላላ ጉባኤውን ጥሪ በሚዲያ የሚያሳውቁ ይሆናል።