ከህወሓቶች ጋር መቀመጥ በህዝብ ደም መቀለድ ነው!
Posted: 03 Dec 2019, 19:51
በቀን 10/03/2012 ዓ.ም ተፅፎ በቁጥር 07642/2019 ወጪ የተደረገው አስገራሚ ደብዳቤ ይድረስ “ለህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ መቀሌ” በማለት ይጀምራል። ጉዳዩ፡- “ስለተጠራንበት ስብሰባ ይመለከታል” በማለት ይቀጥላል። የዚህን ደብዳቤ ትርጉምና ፋይዳ በቅጡ ለመረዳት የተፃፈበትን አውድ በአጭሩ መዳሰስ ያስፈልጋል።
በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን አኑረው የላኩት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ሊቀመንበር አቶ አብዲርሃማን መሃመድ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው ዋና ጉዳዩ ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥሪ የተሰጠ ምላሽ ነው። ህወሓት በመቀሌው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው በስልጣን ዘመኑ በአሸባሪነት የፈረጃቸው የኦብነግ አመራሮች ናቸው።
እንግዲህ በአከባቢው ያለውን የተፈጥሮ ነዳጅ አውጥቶ ለመሸጥ ሲል የኦጋዴን ህዝብን ከምድረገፅ ለማጥፋት ሲሰራ የነበረው፤ ለዚሁ ዓላማ አልሸባብ የተባለ ቡድንን ያደራጀው፣ በሶማሌላንድ በኩል የጦር መሳሪያ እያቀበለ በእጅ አዙር ሀገሩን ያስወረረው፣ የኢትዮጵያን ወታደሮችን ለሞት እየገበረ በፀረ-ሽብር ትግል ስም ከአሜሪካን እና እንግሊዝ ዶላር ሲቀበል፣ በሰላም አስከባሪ ስም ደግሞ ከተባበሩት መንግስታት ይቀፍል የነበረው ህወሓት…። ከቻይና የነዳጅ አፈላላጊ ድርጅት ጋር በመሆን የተፈጥሮ ነዳጅ ለማውጣት በኦጋዴ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የፈፀመው፣ አብዲ ኢሌ የሚባል ንክ ከኤሌክትሪክ ፖል ላይ አውርዶ የሶማሌ ክልል ፕረዜዳንት አድርጎ የሾመው፣ የሶማሌ ህዝብን ለአስራ አምስት አመታት ያህል በመከላከያ ሰራዊት እና በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እንደ ጠላት እያደነ ሲያስገድል የነበረው፤ ንፁሃንን ማሰርና መግደል በውስጡ ያለውን ሰይጣናዊ መንፈስ ማርካት ተስኖት እስር ቤት ውስጥ ጅብና ነብር አስሮ ሲያሰቃይ የነበረው፣… ያለ ምንም ሃፍረት፣ ፀፀት፣ ይቅርታ፣ ተጠያቂነት፣… በጠራው ስብሰባ መገኘት የሶማሌን ህዝብ ማዋረድ ነው። የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ-አውጪ ግንባር ከህወሓት ለቀረበለት የስብሰባ ጥሪ የሰጠው ምላሽ ይህንን መራራ ሃቅ እንዲህ ሲል ገልፆታል፡-
ኦብነግ ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለቀረበለት የስብሰባ ጥሪ በሰጠው ምላሽ ሊሰመርባቸው የሚገቡ ሦስት መሰረታዊ ነጥቦች አሉ። የመጀመሪያው ህወሓት ላለፉት 27 አመታት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በንፁሃን ዜጎች ላይ ለፈጸመው ግፍና በደል ተጠያቂ ሊሆን ይገባል። ሁለተኛ በማንኛውም አግባብ ቢሆን ከህወሓት ጋር ትብብርና ጥምረት መፍጠር ላለፉት 27 አመታት ግፍና በደል በተፈፀመባቸው ዜጎች ደምና እምባ ላይ እንደመቀለድ ይቆጠራል። ሦስተኛ ከህወሓት ጋር በመተባበር የፌደራሊስቶች ግንባር ለመመስረት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ግለሰቦች እና ቡድኖች ህወሓቶች ቀድሞ በፈፀሙት እና ወደፊት በሚፈፀሙት የወንጀል ተግባር ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ እንደመሆናቸው መጠን ከተጠያቂነት አያመልጡም።