Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ተገዶ የተደፈረው ፌደራሊዝም!!!!

Post by Ejersa » 03 Dec 2019, 10:44

ከኢትዮጵያውያን ይልቅ በትህነግ እና ትግራይ ልሒቃን ፈቃድ ሰጭነት የቆመው ሌኒንስታዊ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ያሉ ብሔሮችን ማለቂያ ወደሌለው የልዩነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች ማስገባቱ አንዱ ውርሱ ነው። ብሔር ዘለል ተቋማትን አመንምኖ የልዩነት አጥር የገነባው አውዳሚው ኃይል ኢትዮጵያን ወደ ፍርሰት ጠርዝ በመግፋቱ ረገድ "ተሳክቶለታል" ::

የዚህ ሻምፒዮን የሆነው ታሊባን/ህወሓት በራስ አስተዳደር ሽፋን ተገበርኩት የሚለው ፌደራሊዝም 'ተገዶ የተደፈረ' የአንድ ቡድን ጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት ማሳኪያ እንደነበረ ዛሬ አዲሱን ውህድ ፓርቲ እያፀደቁ ያሉ የክልል አመራሮች እየመሰከሩ ነው።

የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዝደንት "ህወሓት ሳያውቅ የምወስነው ውሳኔ አልነበረም" ብሏል። የሶዴፓ ጽ/ቤት ኃላፊ ደግሞ "በአገራችን 'አጋር' ተብለን ባይታወር ሆነን ኖረናል" ሲል የፌደራሊዝሙን ይስሙላ : የራስ በራስ አስተዳደር ስብከት ሸፍጥ ገልጧል። "በጦርነት ተጎጅ" በሚል የሶማሌ በጀት በትግራይ ልማት ማህበር/ትልማ/ ስም ወደ ትግራይ ሲጋዝ አይቷልና ባይተዋርነቱ ብሔራዊ ቁጭት እንደፈጠረበት በቴሌቭዥን መስኮት በግል ይታይበት ነበር ። የሌሎቹም አጋር ድርጅቶች መሪዎችና አባላት የሃያ ሰባት ዓመቱ ፖለቲካ ቁጭት የባይተዋርነት እና የተበዝባዥነት ስሜት ይታይበታል ። በርግጥም 'አጋር' ሳይሆን ገባር ነበሩ!

ህወሃት በራሱ ፖለቲካዊ ሸፍጥ ያደራጃቸውን ክልሎች ታዳጊና ድጋፍ የሚሹ በሚሉ የስነልቦና የበታችነት ስሜት የሚፈጥሩ ፍረጃዎች ሲያመልኩት እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ። ለዚህም ነው ፓርቲዎቹ 'ገባሮቹ ነበሩ' የምንለው ።

በእነመለስና ስብሐት ጥቂት ቡድን ፈላጭ ቆራጭነት የክልሎቹን ፕረዝዳንቶች ሲሾምና ሲሽር የኖረው ራሱ ትህነግ ነው። ለዚህ ድርጅት አመራር መልካም አቀባበል አላደረክም ተብሎ በግምገማ መገላመጥም ነበረ።

የትግራይ ወገን ተለይቶ "አስተናግዱት" እየተባለ የክልሎቹን ውስን ሀብት ሲመዘብር መኖሩ : የአፋሮች ጨው ቁፋሮና የጋምቤላን መሬት የወረረና የተቆጣጠረ ኃይል የፌደራሊዝም ጠበቃ መስሎ ሲመጣ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላነቱን እንድናስታውስ አስገድዶናል።

እንኳንስ የኢህአዴግ ምክርቤትና ስራ አስፈፃሚ ይቅርና ጥቂት ትህነጋውያን እራት እየበሉ በሚያሳልፉት ውሳኔ በስልክ ይመሯቸው የነበሩ ክልሎች በነበሩበት ፌደራሊዝሙ ተገዶ መደፈሩ ሊታወስ የተገባ ነው።

ለነገሩ ትህነግ የፈጠርኳችሁ ናቸው የሚላቸውን ክልሎች ይቅርና ለኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሽፈራው ሽጉጤን በጓዳ ሲያዘጋጅ እንደነበር አንድ ወዳጄ ያወጋኝን በብርሃነ ፅጋብ መፅሐፍ [2011] ላይ አንበናል።

መቀሌ ድረስ እየጠራ ታዛዡን ጠቅላይ ሚኒስትርነት rehearsal ሲያሰራ መኖሩን ረስቶ የድርጅት ደንብና አሠራር ተጣሰ በሚል ዛሬ ሲያለቅስ እውነተኛ ይመስላል። ማፈሪያ 🙊

ከመጋቢት/2010 ለውጥ ወዲህ እንኳ የፌደራል እና የክልል መንግስት የስልጣን ድርሻን በመጣስ እንደአንድ ሉዓላዊ አገር እየሰራ ባለበት ደረጃ "የፌደራሊስት ጠበቃ ነኝ" ለማለት የሚያሳየው ድፍረት የለመደው ፌደራሊዝሙን አስገድዶ የመድፈር ባህሪው እንዳልተላቀቀው ማሳያ ነው።

ከፌደራሉ መንግስት ድጎማ እየወሰደ ከትግራይ የሚቀርብን ሰሊጥና ወርቅ አግዶ በኮንትሮባንድ እየነገደ: ከፌደራሉ መንግስት በላይ ጦር አደራጅቶና ታጥቆ ÷ የፌደራል መንግስቱን ዘልሎ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እየሠራ "የፌደራሊዝም ጠበቃ ነኝ "ማለትን የመሰለ ስላቅ ከየት ይገኛል⁉️

እንደእውነቱ ቢሆን የፌደራል መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እርምጃ አለመግባታቸው "ለትክክለኛ ፌደራሊዝም የሚከፈል ዋጋ " ተደርጎ እየታየ ከሆነ መጠኑ የበዛ መሆኑና የዚህ ቡድን ጉዳይ ሊለይለት የሚገባ ነው።

በርግጥ ትህነግ "ስላልቻሉን አርፈው ተቀመጡ : ትግራይን መድፈር ከታሪክ አለመማር ነው" የሚል ፉከራ በነጌታቸው ረዳ ልፋፌ ሲሰማ ÷" እንኳንስ ለዐቢይ አህመድ መንግስት ለየትኛውም ኃይል የሚመጥን የጦር ዝግጅት አድርገናል" ብሎ ደብረጽዮን በአደባባይ ሲያውጅ : ፌደራሊዝም ዛሬም እንደትናንቱ ተገዶ መደፈሩን ያሳያል።

የፌደራል መንግስትን ስልጣን ተጋፍቶ የጋራ ህልውና ስጋት ላይ ተሰማርቶ ህግ ይከበር: "ፌደራሊስት ነን" እያለ ሲያላገጥ ህዝብ ማገናዘብ አይችልም ከሚል ንቀት እና 'ዐይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ' ነው። የDefacto state ከበሮ እየደለቁ ፌደራሊዝሙ ተደፈረ ከማለት በላይ ስላቅ የት አለ? 🤔

ትህነግ ትናንትም ሆነ ዛሬ ፌደራሊዝሙን አስገድዶ ሲደፍር እና "አሃዳዊነት መጣባችሁ" እያለ ሲሳለቅ እንደኖረ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊነቃ ይገባል።
ሙሉዓለም ገ/መድን

EthioRedSea
Member
Posts: 4089
Joined: 31 Aug 2019, 11:55

Re: ተገዶ የተደፈረው ፌደራሊዝም!!!!

Post by EthioRedSea » 03 Dec 2019, 11:17

USA and The West raped Ethnic Federalism by proxy (using Eritrea and Egypt) to stop China's control of Ethiopia and africa.

Ethnic Federalism has brought many benefits too. Ethnic groups that were seen as sub-humans have their own territory and government. There were some mistakes, but in general Ethnic Federalism was the foundation for democracy in Ethiopia. Ethiopia needs to have more working languages. We need to modify Ethnic Federalism so that we focus on our common characters as Ethiopians.

Post Reply