Yared Tibebu
19 hrs ·
ሰበር ዜና
የኢህአዴግን መፍረሰና የብልፅግና ፓርቲን መዋሀድ ከፈረሙት 8 የድርጅቶች መሪዎች መሀል፣ በሀገሪቱ የሥራ ቋንቋ በአማርኛ የፈረሙት ብቸኛ መሪ አቶ ደመቀ መኮንን መሆናቸውን አይቼ ገረመኝ ። የገረመኝ ነገር፣ ከስምንቱ የብልፅግና ፓርቲ መሪዎች መካከል 6ቱ ሙስሊሞች፣ 2ቱ ከሙስሊም ወላጆች የተወለዱና አንድም ሙሉ ክርስቲያን አለመገኘቱ በአጋጣሚ ነው ወይስ በዲዛይን የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል። አብላጫው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኝ፣ እጅግ አብላጫው ደግሞ ክርስቲያን በሆነች ኢትዮጵያ ውስጥ ከአግላይነት ወደፍትሀዊነት ተሸጋገርኩ የሚል ገዢ ፓርቲ በወሳኝ አመራር ቦታ ላይ አንድም የኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሌለው መሆኑ፣ ለ29 ዓመታት የተዋህዶ ክርስቲያኖችን ከወሳኝ የሃገሪቱ ህይወት ለመነጠል የተሰራውን ብልግና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፣ አፋጣኝ እርማት ያስፈልገውም ይመስለኛል። የተዋህዶ ክርስትና አማኞች ከቁጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ሚና በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲጫወቱ መጠየቅ የፍትህና እኩልነት ጥያቄ ነው። ብልፅግና ፓርቲ የማነው፣ የኢትዮጵያ ወይስ...? ለዝርዝሩ መረጃውን ከሥር ይመልከቱ።
