Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
wazzupdog
Member
Posts: 1911
Joined: 16 Jun 2018, 22:10

Warning to Lemma Megersa

Post by wazzupdog » 30 Nov 2019, 18:36

......There are reports Lemma Megersa is in bed with terrorist Ja-war Mohammed. Lemma needs to know that a terrorist's buddy is another terrorist. Taking part in Ja-war's ethno-jihadist campaign against christians and non-oromos will have severe personal consequences for Mr Suse......

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: Warning to Lemma Megersa

Post by Maxi » 30 Nov 2019, 18:40

ለማ መገርሳ በአብይ አሀመድ እና በ"ብልፅግና ፓርቲ" ላያ ያፈነዳው ቦም!!!! ሙሉ ቃለ መጠየቅ!! :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ለማ መገርሳ ከVOA ጋር ያደርገው ሙሉ ቃለመጠየቅ

wazzupdog
Member
Posts: 1911
Joined: 16 Jun 2018, 22:10

Re: Warning to Lemma Megersa

Post by wazzupdog » 30 Nov 2019, 18:54

.........Digital qimal Maxi, you've been jumping up and down like a monkey ever since the news broke. I guarantee you it won't help your looter woyanes one bit..........

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: Warning to Lemma Megersa

Post by Maxi » 30 Nov 2019, 19:00

Digital qimal wazzupdog :lol: :lol: :lol: :lol:


wazzupdog
Member
Posts: 1911
Joined: 16 Jun 2018, 22:10

Re: Warning to Lemma Megersa

Post by wazzupdog » 30 Nov 2019, 22:17

አማራ ሚዲያ ማዕከል / Amara Media Center
10 hrs ·
ከአቶ ለማ መቀነስ ባሻገር....!

አማራ ሚድያ ማዕከል/አሚማ/
ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

በሕዝባዊ ማዕበል ወደፊት ከመጡትና አጋጣሚውን ተጠቅመው ኢህአዴግን ከህወሓት መርነት ወደ ኦህዴድ መርነት ካሸጋገሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት አንዱና ፊት አውራሪ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ መሆናቸው ይታወቃል።

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትና የአሁኑ የኢፌደሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" በሚል ንግግራቸው ይታወቃሉ።

አዎ ለአቶ ለማ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፤ ሱስ ደግሞ በተፈለገው ጊዜ የሚለቅ ከድብርትና ከችግር ለመውጣት የጨነቀ'ለት የሚገቡበት መሸጋገሪያ ነው።

አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ በቅኔ ሳይሆን በቀጥታ ቋንቋ መደመርን አልደግፍም በማለታቸው የተለዬ ነገር አልተፈጠረም።
የተለዬ ያስመሰለው የሕዝቡ አረዳድ ነው

አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው "የለውጥ ሀዋርያ" እየተባሉ በሚወደሱበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ዘረፋና ሌሎች ብዙ ወንጀሎች ሲፈፀሙ ማስቆም አልቻሉም ወይም አልፈለጉም።

በቡራዩ በጋሞ ተወላጆች ላይ የተደረገው ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሶማሌ ብሔር ተወላጆች ላይ የደረሰው ግድያና ማሳደድ፣ በአማራ፣ በጉራጌና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው ተመሳሳይ ግድያና ማፈናቀል ሲፈፀም የክልሉ አስተዳዳሪ የነበሩትና ኢትዮጵያዊነትን በተራ ሱስ የጠሩት "የለውጥ መሪ" እየተባሉ የተወደሱት አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የሕዝብ ስብጥር ለመቀየርም በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ቤቶችን በመሥራት ከምሥራቅ ኦሮሚያ ዜጎችን በገፍ በማምጣት ሲያሰፍሩና ይኸንን ተግባራቸውን በተመለከተም በአንድ መድረክ ላይ "ሥልጣን ላይ የተቀመጥነው የገብርኤልን ጠበል ልንዘክር ሳይሆን ኦሮሞን ልንጠቅም ነው" ብለዋል። ችግሩ ያለው ኦሮሞን ከመጥቀማቸው ሳይሆን በሌሎች ኢትዮጵያውያን መቃብር ላይ ካልሆነ ኦሮሞ አይጠቀምም ወደሚል ፅንፍ የወጣ ሀሳብን ወደሚያራምዱት የፅንፍ ቡድኖች መግባታቸው ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን በሽንገላ ወሬ ስለምንሸወድ እንጅ አቶ ለማ ከጅምሩም ጀምሮ በኢትዮጵያዊነትና በእኩልነት ለማመናቸው አንድም ተግባራዊ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም።

በአዲስ አበባ ከተማም ከመታወቂያ እደላ ጀምሮ ያለውድድር የሥራ ቅጥር፣ ለከተማው ተወላጆች የተመደበን የወጣት የብድር ፈንድ ለአንድ ወገን መስጠት፣ የከተማው ነዋሪ ከዕለት ጉርሱ ቆጥቦ ያስገነባውን ኮንዶሚንዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ክፍያ ለአንድ ወገን ከነ ልጅ ልጆች ማደልና ሌሎች የተረኛና አፓርታይድ አካሄዶች የነ ለማ ቡድን በአዲስ አበቤዎች ላይ እያደረገው የሚገኘው አሻጥራዊ አካሄድ አንድ አካል ነው።

ይህ ሁሉ ሲሆን አሜን ብሎ በመቀበል ድጋፍ የሚያደርግና ለአፓርታይዳዊ አካሄዱ ዕውቅና የሚሰጥ ሰው የምር ስለሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰውነቱ እኩል ያስባል የሚለውን መጠየቅ ግድ ይላል።

ኢህአዴግ ከግንባር ወደ ውህደት ለመምጣት ባቀረበው ሀሳብ መሠረት ከሀሰተኛዋ ፌደራሊስት ህወሓት በስተቀር ሌሎቹ የግንባሩና አባላትና አጋር ፓርቲዎች ወደ ውህደቱ እየገቡ ይገኛሉ። አዲሱ የብልፅግና ፓርቲም "ሰው በሰውነቱ እንጅ በብሔሩ አይዳኝም" የሚል እንድምታ እንዳለው ተነግሯል።

በሀገራችን እውነተኛ ፌደራሊዝም የለም እንጅ ሀቀኛ ፌደራሊዝም ቢኖር የሚጠላ ባልነበር፤ ምናልባት ትህነግንና አምሳያዎቿን ሳያካትት።

ነገር ግን በብሔር ፌደራሊዝም ሥም ለባለፉት 27 ዓመታት ሀገርን ሲዘርፉና ሲገርፉ፣ ሲያዋርዱና የፈለጋቸውን ሲሠሩ የነበሩት ትህነጋውያን በሕዝብ ማዕበል ከሥልጣን ተወግደዋል።

ምንም እንኳን ሕወሃት ከስልጣን ቢወገድም በባለፈው አንድ ዓመት በነበረውና "የለውጥ ጊዜ" የሚል ስያሜ በተሰጠው ዓመት ለውጡ ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ ሳይሆን ከሕወሃታዊ አምባገነንነት ወደ ኦህዴዳዊ ፋሽስትነት የተሸጋገርንበት የተረኝነት ዘመን ለመሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ማዬት በቂ ነው።

በዚህ የተረኝነት አካሄድ የሀገሪቱ ክልጣን ከህወሀት ወደ ኦህዴድ ተሰጋግሮ የህወሓት አምባገነናዊ ሥርዓት ተሻሽሎ በፅንፈኛና ሥርዓት አልባ መንጋ ተቀይሮ ብዙ ዘግናኝ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ይገኛሉ።

ይኸንን የተረኝነትና የአምባገነናዊ የመንጋ አካሄድ ያስቆማል የተባለለት የብልፅግና ፓርቲ ወደ ተግባር ከመግባቱ ማግስት የዛኔው የለውጥ መሪ እየተባሉ የተወደሱት አቶ ለማ መገርሳ "መደመርን አልደግፍም፣ ደግፌም አላውቅም መሆን ካለበትም ጊዜው አይደለም" ማለታቸው ምንን ያመላክታል?

በነገራችን ላይ አቶ ለማ ለቪኦኤ የሰጡት ቃለ መጠይቅ ከሀሰተኛዋ ፌደራሊስት ከህወሓት ጋር ተመሳሳይ የሆነ አቋም ነው። የሀገርን መከላከያ ሠራዊት የሚያክልን ትልቅ ተቋም እየመሩ ከመንግስት መርህና ፍልስፍና በተቃራኒ ቆመው ከአፈንጋጯ ትህነግ ጎን የተሠለፉት አቶ ለማ የቀድሞው ኢህአዴጋዊ አሠራር ከህወሓት ወደ ኦህዴድ ተቀይሮ እንዲቀጥል የፈለጉ ይመስላል።

በዚህ አቋማቸው የመከላከያ ተቋሙን ለግል ሀሳባቸው በመጠቀም ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይከቱት ጥንቃቄ የሚያሻው ይሆናል።

ዜጎች በብሔራቸውና በሐይማኖታቸው ተለይተው በመንጋ ፍርድ በሚዘገንን መልኩ የሚገደሉበትን ክልል ወክለው መከላከያን ያክል የሀገር ተቋም እየመሩ የሚገኙት አቶ ለማ መገርሳ፤ በሚመሩት መከላከያ ዜጎችን ከሞት መታደግ ሲገባቸው አሁንም በዜጎች ላይ ተመሳሳይ መገደልን ሊያመጣ የሚችልና የፖለቲካ ትኩሳቱን የሚያጧጡፍ ንግግር ማድረጋቸው በኦሮሚያ ክልል ለሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ተጨማሪ ስጋትንና አደጋን መፍጠሩ አይቀሬ ነው።

ለኢትዮጵያ "ከእኔ በላይ ላሳር" ሲሉ የነበሩት ሰው ዛሬ ወደጎጥ ወርደው ሕዝብ ካስቀመጣቸው ዙፋን ላይ ተንሸራተዋል። ለጊዜው ፅንፈኛና በጥላቻ የሰከሩ መንጋዎች ከአቶ ለማ ጎን ሊሠለፉ ይችላሉ። ፍፃሜው ግን ለሀገር አይበጅም። ፖለቲካ እንዲህ ነው፤ ትናንት የታመነው ዛሬ ይከዳል፣ አሻጋሪ የተባለው መሀል ውቅያኖስ ውስጥ ይጥላል። በማንም ጥገኛ ላለመሆንና ችግሮችን ሁሉ በራስ አቅም ለመሻገር ከአምሳያ ጋር ተደራጅቶ የራስን ነገ በራስ እጅ መፃፍ ከሀሰተኛ አሻጋሪዎችና በሚዋዥቅ አቋማቸው ከሚመጣ የሥነ-ልቦና ስብራት መዳን ይቻላል።

"ለራስ ማን እንደራስ" እንደሚባለው የሰው የሰው ነው፤ የሰው መሆኑን አሳይቷል። የራስን መሪ መፍጠርና ጠብቆ መያዝ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ይሆናል።


Post Reply