በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል።
Posted: 30 Nov 2019, 08:56
ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሀመድ ድጋፋቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል። ጃዋር መሀመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች እና በአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟረ ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። ዛሬ በኑርንበርግ ከተማ ድጋፋቸውን ለመግለፅ አደባባይ የወጡት ኢትዮጵያውያን የኦነግን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ባንዲራዎችም ይዘው ተስተውሏል።



