Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

አስቸኳይ መረጃ ለአፋር ብ/ክ/መንግሥት እና ህዝብ!!!!

Post by Ejersa » 28 Nov 2019, 18:09

መረጃ: ህወሓት በቅርቡ እርቅ በፈፀሙት በአፋርና ኢሳ ማህበረሰብ መካከል ከባድ ግጭት እንዲቀሰቀስ የመጨረሻ ምዕራፉን ዛሬ አጠናቋል። ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል በፌዴራሊስት ግንባር ስብሰባ ስም የፕሌን ቲኬት ተቆርጦላቸው መቀሌ የተገኙ አካላት በሙሉ የሽብሩ ተዋናይ እንደሚሆኑ ታውቋል።በተለይ ከሶማሌ ክልል በኩል (ሶዴፓ ለውህደት እያካሄደ ባለው ጉባኤ ምክንያት ባይገኝም) የግጭቱ መሪ ተዋናይ አዳም ፋራህ መሆኑ ተገለጿል።

ከአፋር በኩል ግጭት ለመቀስቀስ ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለበት ኮማንደር #ማህሙድ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል።ሁለቱም በዚህ ሰዓት ከህወሓት ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ሊመስለን ይችላል።መረጃው እንደሚያረጋግጠው ግን ነገሩ ፍፁም ተገላብጦሽ ነው።የሶማሌው አዳም ፋራህ ምንም እንኳ ከህወሓት ጋር በአካል በስብሰባው ላይ ባይገኝም በተወካዮቹ እንዲሁም በስልክና በኢሜል እንደሚገናኙ ያረጋግጣል።ከአፋር በኩልም ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለበት ኮማንደር ማህሙድ ከእስር እንዲፈታ ህወሓት የሞት ሽረት ማድረጉን መረጃው ያረጋግጣል።ተልዕኳቸው በሶማሌና በአፋር ክልል መካከል የብሔርና የድንበር ግጭት ለመቀስቀስ መሆኑ በመረጃው ተገልጿል።

በመረጃው መሠረትም፦ ከአፋር ክልል ዞን-3 በሙሉ የሽብርተኞች ኢላማ ውስጥ መሆኑንና በተለይ አዋሽ area ከኢሳ አልፎም #ከኦሮሞ ጋር የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።በመሆኑም የአፋር ብ/ክ/መንግሥት የክልሉን ሰላም ከመቸውም ጊዜ በላይ በመጠበቅ ከወዲሁ ለህዝቡ ደህንነት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ ዘንድ በጥብቅ አሳስባለሁ።የክልሉ ህዝብም ለአጥፊዎች በተለይ የብሔርና የሀይማኖት ግጭት እንዲቀሰቀስ ከሚፈልጉ ከማናቸውም የጥፋት ሀይሎች አሉባልታ ወሬ ራሱን በመጠበቅ፣ ለሰላሙ ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነት ዘብ እንዲቆሙ ዘንድ ኢሄ መልዕክት ተላልፋል‼