Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና: የሀረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሀብሊ) ከኢህአዴግ የቀረበለትን የውህደት ጥያቄ ተቀበለ!!!!

Post by Ejersa » 27 Nov 2019, 01:09

የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ከትላንት ህዳር 15/2012 ጀምሮ ሲያካሄድ በነበረው 11ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶች ውህደትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።

ጉባኤው በዛሬ ህዳር 16/2012 ከሰአት በኋላ ውሎው በውህድ ፓርቲው ህግና ደንብ ዙርያ እና አደረጃጀት እንዲሁም በፓርቲው መርህ፣ አሰራር ዙርያ በሰፊው መክሯል። በዚህም የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ከኢህአዴግ የቀረበለትን የውህደት ጥያቄ መቀበሉን በ11ኛ መደበኛ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ አፅድቆ ተቀብሏል።

በጉባኤውም በኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ውህደት ሀብሊ የወከለው ማህበረሰብ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ መሆኑን አፅዕኖት በመስጠት ተወያይቷል። ድርጅቱም እንደ ሀገር ሊያበረክት የሚገባውን አስተዋፅኦ ለማድረግና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በባለቤትነት ለመሳተፍ እና ለመወሰን የተነፈገውን እድል የሚያጎናፅፍ መሆኑን ተጠቁሟል። የኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ውህደት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት ሁሉም ዜጋ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ለመወሰን እድል ያጎናፀፈ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም የክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግሥታዊ መብትን የሚያጠናክርና የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም በጉባኤው በስፋት ቀርቦ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ድርጅቱ በጉባኤው የአዲስ የድርጅት አመራሮችን ምርጫ በማካሄድ 30(ሰላሳ) የማዕከላዊ ኮሜቴ አባላትን እና 9(ዘጠኝ) የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላትን ከነ ተጠባባቂያቸው በመምረጥ ጉባኤውን ዛሬ ማታ አጠናቋል።