ሰበር ዜና: ህዳር 24 -25/2012 በመቀሌ ከተማ የፌዴራሊስቶች ግንባር ይመሰረታል!!!!
Posted: 25 Nov 2019, 13:28
ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ህወሃትና ተላላኪዎቹ በሚያካሂዱት ስብሰባ የፈደራሊስቶች ግንባር እንደሚመሰረት ከወደ መቀሌ የደረሰን መረጃ ያስረዳል። ግንባሩ የሚመሰረተው በህወሓትና ተላላኪዎቹ ሲሆን የግንባሩ ዓርማ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ በሚጋልብ ጉማሬ መሳይ ፈረስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የግንባሩ ፕሮግራም አብዮታዊ_ዴሞክራሲ ሲሆን የመተዳደሪያ ደንቡ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ይባላል። በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ያለው የስልጣን ክፍፍል ፍፁም ፍትሃዊና የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት የሚያረጋግጥ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

