Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የጭቆና ሰይጣን ሳይገድል አይለቅም‼

Post by Hameddibewoyane » 24 Nov 2019, 14:57

ኦዴፓ፣ አዴፓና ደህዴን ህወሓትን ትተው የራሳቸው የሆነ የፖለቲካ ፕሮግራም እና የመተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ቢጀምሩ በአዋጁ መሰረት መብታቸው ነው። እንደ አዲስ ባረቀቁት የፖለቲካ ፕሮግራምና የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ውህደት ለመፈፀም ከፈለጉ መብታቸው ነው። በኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ አዋጅ አንቀፅ 93 በተደነገገው መሰረት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት መፈፀም እንደሚችሉ ይገልፃል። ፓርቲዎቹ ውህደት ለመፈፀም የሚያቀርቡት ማመልከቻ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት አለበት፤

1ኛ) እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፓርቲው ጉባኤ ውህደቱን የተቀበለ ስለመሆኑ የሚገልፅ ውሳኔ፣
2ኛ) ፓርቲዎቹ ስለ ውህደቱ ዝርዝር ጉዮች ያደረጉት የፅሁፍ ስምምነት እና
3ኛ ፓርቲዎቹ ሲዋሃዱ የሚኖራቸው አዲስ ስምና በአዋጁ አንቀፅ 67 የተዘረዘሩ ሰነዶች ናቸው።

ከላይ በተገለፀው መሰረት የህወሓትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም ሲያስፈፅሙ የነበሩት ሦስቱ የኢህአዴግ አባል ድርቶች የራሳቸው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ መቅረፃቸው ትክክልና አግባብ ነው። ህወሓት ከተቀሩት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶ ጋር መዋሃድ ከፈለገ አሮጌውን የፖለቲካ ፕሮራም እና የመተዳደሪያ ደንብ መጣል አዲስን ፕሮግራምና ደንብ በማርቀቅ ሂደት ውስጥ መሳተፍ አለበት። በመቀጠል በፕሮግራሙና ደንቡ ላይ ተወያያቱ በአብላጭ ድምፅ የፀደቀውን መቀበል ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ከተሳነው ደግሞ ሦስቱ ውህደት ሲፈፅሙ ህወሓት ደግሞ የራሱን ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ እና አባላት ይዞ ከግንባሩ ይወጣል።

ውህደቱን ያልተቀበለው ህወሓት ከግንባሩ ከወጣ በኋላ ሲፈልግ ለብቻው ወይም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምረት፣ ግንባር አሊያም ውህደት መፈፀም ይችላል። በአንፃሩ የተዋሃዱት ሦስቱ ፓርቲዎች ቀድሞ የነበራቸውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለምርጫ ቦርድ በመመለስ አንድ ስምና አርማ ይኖራቸዋል። ቀድሞ የነበራቸውን የመተዳደሪያ ደንብ በመተው በአዲሱ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ይመራሉ፣ የፓርቲዎቹ አባላትም የአዲሱ ፓርቲ ይቀላቀላሉ። ከዚህ በተጨማሪ በአዋጁ አንቀፅ 92 መሰረት የውህደቱ ውጤት የሆነው አዲሱ ፓርቲ የተዋሃዱት ፓርቲዎች ወራሽ ይሆናል፣ የተዋሃዱት ፓርቲዎች መብትና ግዴታ ይተላለፍለታል።
በአዋጁ አንቀፅ 92 ንዕስ አንቀፅ 3 መሰረት ውህደት የፈጠሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባል የነበረና በማናቸውም ደረጃ ያሉ ምክር ቤቶች ተመራጭ ሆኖ በማገልገል ላይ የነበረ ሰው በውህደቱ በተፈጠረው የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኖ መቀጠል የማይፈልግ ከሆነ የግል ተመራጭ እንደሆነ ተቆጥሮ የቀረውን የምርጫ ዘመን ያጠናቅቃል።

በመጨረሻም በሕገ መንግስቱ መሰረት አንድ የምክር ቤት ተመራጭ ተጠያቂነቱ ለህዝብ፣ ለህገ መንግስቱ እና ለህሊናው እንደሆነ ይገልፃል። ላለፉት 27 አመታት የምክር ቤት ተመራጮች ተጠያቂነታቸው ከህዝብ፣ ህገ መንግስቱ እና ህሊናቸው ይልቅ ለፓርቲያቸው እንደነበር በተግባር አይተናል። አንድ የህወሓት አባል የሆነ ተመራጭ ተጠያቂነቱ ለመረጠው ህዝብና ለፓርቲው ሊሆን ይችላል። አንድ የኦዴፓ፣ አዴፓ፣ ደህዴን ወይም አጋር ድርጅቶች አባል የነበረ የምክር ቤት ተመራጭ ከህዝብ፣ ህገ መንግስቱ እና ህሊናው ይልቅ በህወሓት ለተነደፈው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም እና ለዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሰራር ተገዢ የመሆን ግዴታ እንደነበረበት አይዘነጋም።

የህወሓትን የበላይነት አሊያም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም መቃወም ቀርቶ በክፉ ያነሳ የምክር ቤት ተመራጭ ሆነ የፓርቲ አመራር ትላንት የት እንደደረሰና ምን እንደደረሰበት፣ ዛሬም የት እንዳለ እናውቃለን። ያ የባርነት ዘመን እንዳያንሰራራ ሆኖ ተንኮታኩቶ ወድቋል። እነደ እናንተ በወታደራዊ ኃይልና ጉልበት ሳይሆን በዕውቀትና የሃሳብ የበላይነት ተሸንፎ ሞቷል። ልክ እንደ ቀድሞ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረት ውድቀት ከማፋጠን የዘለለ ፋይዳ የለውም። ከላይ በተገለፀው መሠረት ህወሓቶች የኢህአዴግ ውህደት ለመቃወም ሆነ ለማደናቀፍ የሚያስችል ምንም ምክንያት የላቸውም። ነገር ግን “የጭቆና ሰይጣን ሳይገድል አይለቅም” እንደሚሉት ጨቋኝና ጨካኝ ያደረጋቸው ሰይጣን የራሳቸውን መቃብር እያስቆፈራቸው ነው።