Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Ejersa
- Member
- Posts: 3978
- Joined: 05 Nov 2019, 10:39
Post
by Ejersa » 23 Nov 2019, 18:27
እንደሚታወቀው የትህነግ ሰዎች አፋር ክልልን የአመጽ ቀጠና ለማድረግ ሴራወችን አቅደው በትላንትናው እለት በአቶ ስብሃት ነጋ፣ ኮሌኔል ነጋሲ፣ አሊ አብደላ የአብዴፓ ድርጅት ጽ/ቤት ም/ል ሃላፊ የነበረና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው ሰወች በሰመራ ከተማ አርዲ ሆቴል ስብሰባዎችን እያደረጉ መሆናቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
ከዚህ በተጨማሪ ትላንት ህዳር 12/12 አመሻሹ ላይ 2 ሰዓት ገደማ ጀምሮ ደግሞ የትግራይ ቴሌቪዥን፣ ዲጂታል ወያኔና ሌሎች ጽንፈኛ ጋዜጠኞችና ሚዲያዎች ጭምር በአርዲ ሆቴል ተሰባሰብው ስለቀጣይ ተግባራት እየመከሩ እንደሚገኙ መረጃወች ያሳያሉ። ዱኪሂና (የአፋር ወጣቶች) አካባቢህን በተጠንቀቅና በንቃት ተከታተል፤ መረጃውንም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅና በማጋራት የትህነግና ግብረ አብሮቿን ሃገር የማተራመስ እቅድ አሳውቅ!!!

-
Hameddibewoyane
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42
Post
by Hameddibewoyane » 23 Nov 2019, 18:39
አዲሱ ውህድ ፓርቲ የአገር አንድነትን ከማጠናከር ባለፈ የብሄር ብሄረሰቦችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የማይጋጭና እያንዳንዱ ብሄርና ብሄረሰብ ባህልና ቋንቋውን እንዲያበለጽግ የሚያስችሉ አሰራሮችና ደምቦችን በማካተት ለዘመኑ ትውልድ እና ንቃተ ኅሊና በሚመጥን መልኩ ሆኖ የተመሰረተ እንደሆነም ከሰማናቸው ማብራሪያወችና ከፕሮግራሙ ለመረዳት ችለናል። ከኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እድገትና መስፋፋት ጋር ተያይዞ ዓለም ወደ አንድ መንደርነት እየሄደችና የዓለም ሕዝቦች የበለጠ ቅርብ እየሆኑ ባለበት ዘመን የኢትዮጵያ ብሄርና ብሄረሰቦች በአንድ መንግስት ጥላ ስር ሆነው ወጥ የሆነ ኅብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅት መስርተው መንቀሳቀስ ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር በመሆኑ ውህደቱ በዚህ በኩል የሚደነቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ብሄሮችና ብሄረሰቦች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች አንዳቸው ከሌላው ተለያይተው በተናጠል ለየብቻ ተፈናጥረው መኖር የማይችሉ ከመሆናቸው በላይ በሚኖራቸው መስተጋብር በእኩልነት መርህ በመከባበር ተዋዶና ተፋቅሮ ከመኖር ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም። እንዲህ ዓይነቱን ማኅበረሰብ የሚመራ መንግስትና ፓርቲ ደግሞ አወንታዊ ሚናወችን በመጫወት የማኅበረሰቡ መስተጋብር የተቀና እንዲሆን ኢህአዴግ በአዲስ መልኩ ውህደት ፈጥሮ የብልጽግና ፓርቲን መመስረቱ ታላቅና በሳል የፖለቲካ እርምጃ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ነው።
እንግዲህ የገዥው ፓርቲ የበላይ አመራሮች የሆኑት ጠሚ ዓቢይ አህመድ፣ ም/ጠሚ ደመቀ መኮነን እንዲሁም የእያንዳንዱ ግምባርና አጋር ፓርቲ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች ከትህነግ እና መሰሎቹ በኩል ያለባቸውን ጫናና እጅግ በክፋትና በተንኮል የተሞላ አፍራሽ አካሄድና ሴራ ለመቋቋም ይህን ውህደት ለመፈጸም በመቻላቸው እጅግ የሚደነቅ ተግባር እንደሆነ ለማስቀመጥ እወዳለሁ። ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና በራስ መተማመን የሚጠይቅ ነገር ከመሆኑም በላይ በብሄር ፖለቲካ ጥርሱን የነቀለው ህወሓት የነበረውን ተቋማዊ የበላይነት ለማስቀጠል ከዚህ የተሻለ አማራጭ ስለሌለው ይህ የውህደት ፕሮጀክት እንዳይሳካ ከመሬት በታች ባለው አቅሙ ማድረግ የሚችለውን ነገር ሁሉ በማድረግ ሊያሰናክላቸው ባለመቻሉ ነው። ከዚህም በላይ ያለፉት 50 ዓመታት ጫፍና ጫፍ የቆሙ በባላንጣ የሚተያዩ የፖለቲካ እሳቤወችን ገልብጦ በመጣል፣ ውስንነታቸውን በማስወገድ የእሳቤወቹን መልካምና ጠቃሚ ጎኖች ወሰዶ ወደ ማዕከል መጥተው ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ርዕዮትና አቅጣጫ የሚከተል የመጭውን ዘመን ፖለቲካ ለመወሰን አቅም ያለው አሳታፊ ኅብረ ብሄራዊ ወጥ እና አንድ ፓርቲ መመስረት እንደ ታላቅ ተግባር የሚቆጠርና ራሳቸውንም በፖለቲካ ታሪካችን ስማቸው ጎልቶ እንዲጻፍ የሚያደርግ ነው። በዚህ የውህደት ፕሮጀክት ድርሻ ያለውና ሚናውን በቅንነት የተወጣ አመራርና ባለሙያ ሁሉ መልካም ነገር እንደሰራ ሊቆጥረው የሚገባ ነው።
Ejersa wrote: ↑23 Nov 2019, 18:27
እንደሚታወቀው የትህነግ ሰዎች አፋር ክልልን የአመጽ ቀጠና ለማድረግ ሴራወችን አቅደው በትላንትናው እለት በአቶ ስብሃት ነጋ፣ ኮሌኔል ነጋሲ፣ አሊ አብደላ የአብዴፓ ድርጅት ጽ/ቤት ም/ል ሃላፊ የነበረና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው ሰወች በሰመራ ከተማ አርዲ ሆቴል ስብሰባዎችን እያደረጉ መሆናቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
ከዚህ በተጨማሪ ትላንት ህዳር 12/12 አመሻሹ ላይ 2 ሰዓት ገደማ ጀምሮ ደግሞ የትግራይ ቴሌቪዥን፣ ዲጂታል ወያኔና ሌሎች ጽንፈኛ ጋዜጠኞችና ሚዲያዎች ጭምር በአርዲ ሆቴል ተሰባሰብው ስለቀጣይ ተግባራት እየመከሩ እንደሚገኙ መረጃወች ያሳያሉ። ዱኪሂና (የአፋር ወጣቶች) አካባቢህን በተጠንቀቅና በንቃት ተከታተል፤ መረጃውንም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅና በማጋራት የትህነግና ግብረ አብሮቿን ሃገር የማተራመስ እቅድ አሳውቅ!!!
-
Digital Weyane
- Member+
- Posts: 9672
- Joined: 19 Jun 2019, 21:45
Post
by Digital Weyane » 25 Nov 2019, 16:56
አፋር የትግራይ ግዛት የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ኡኛ ዲጂታል ወያኔ ራሳችንን አዋሽ ብለን የሙንጠራው ሰዎች ይህንን ሃቅ ኡንዲያውቁልን ቡለን ነው። ኡናሽንፋለን።