የነፈፍጠኛ ልጆች አለንበት ለማለት የሚያወሩት ትግል ካለም ከፊሉን ኦሮሞ በመተታቸው አፍዘው አደንዝዘው በሌላው ኦሮሞና ጭቁን ህዝቦች ላይ ያነሳሱትንና እነርሱ ተጠቃሚ የሆኑበትን ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ የነፈፍጠኛ ልጆች (ኦሮሞ ካባረራቸው በኃላ) የሚታገሉት በአብዛኛው በሚዲያ እንጅ መሬት ላይ የወረደና የተመዘገበ የትጥቅ ትግል የላቸውም፡፡ ለምሳሌ የሲዳማን የነጻነት ትግል ና ሪፈረንደም ለማካሄድ በተደረገው የትግል ጉዞ ውስጥ የሀበሻ ሚዲያ (ESAT, Ethio 360 እና የአማራ ሚዲያ በሙሉ) ተካፍለዋል፡፡ የሞት ሽረት ትግላቸው የሲዳማ ሪፈረንደም እንዳይካሄድ ነበር፡፡ ሪፈረንደሙ ከተካህደ ደግሞ የሀዋሣ ከተማ ከሲዳማ እንድትለይ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይና ያላዘቡት እውኔታ አልነበረም፡፡ ሁለቱም አልተሳካላቸውም፡፡ እንደ ቅድሜ ሪፈረንደም ወሬና ዛቻቸው እኔ የጠበቅሁት ሲዳማ ነጻነቱን ከመረጠ እነርሱ በጦርነት ምድሪቱን ያቀውጣሉ የሚል ነበር፡፡ አጅሬ ወሬ ዞር አሉና ምንም ሠያፍሩ አይናቸውን ጨፍነው መካሪ ሁነው ቀረቡ፡፡ ለካስ ወሬዎቹ በዘልማዳቸው የተፈበረኩ እንጂ የሚያስከትሉት ውጤት እንዳሌለ እነርሱም ያውቁት ኖሮአል›፡፡
ከዚህ ተሞክሮ የምንማረው ሌሎች መልካም ነገሮች አሉ፡፡ በተለይ ለቅማንትና አገው ሕዝቦች መልካም ዜና ነው፡፡ ማንነታችሁን ለማጉላት አድራሻና ማንነት የሌላቸውን ወሬኛ አማሮች ቸል ብላችሁ የልባችሁን ማከናወን ነው፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ አነርሱም ፊትለፊት አይዳፈሩም፡፡
ድል ለጭቁን ሕዝቦች!