ኢህአዴግ ከሚባለው ህወሃት ምርኮኞቹን ሰብስባ ከፈጠረችው ግንባር ወጣ የሚባለው ማለው?
ህወሃት ወይስ ኦህዴድ + ብአዴን + ደኢህዴን?
እንደኔ ግንዛቤ ከሆነ ከኢህአዴግ በመውጣት አዲስ የ"ብልግና ፓርቲ" የሚባል የመሰረቱት ኦህዴድ + ብአዴን + ደኢህዴን ናቸው። ስለዚህ ህወሃት ኢህአዴግ የሚለው የድርጅት ስም እንደያዘች የመቆየት መብት ያላት ይመስለኛ። ህወሃት ኢህአዴግ የሚለውን ስም ይዛ ልትቆ ከሚያስችሏት በርካታ ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ.-
1ኛ. ኢህአዴግ የሚለውን ግንባር አፍርሰው አዲስ የ"ብልግና ፓርቲ" የመስረቱት ኦህዴድ + ብአዴን + ደኢህዴን እንጅ ህወሃት ባለመሆኗ
2ኛ. ከመጀመርያውም ኢህአዴግ የሚለውን ስብስብ ምርኮኞችን በመሰብሰብ የፈጠረችው ህወሃት ስለሆነች ከምርኮኞቹ የበለጠ የኢህአዴግ የባለቤትን መብት ወይም "ቬቶ ፓዎር" ያላት ህወሃት በመሆን ነው።
እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታችሁን ስጡበት።