ኢህአዴግ በይፋ ዛሬ ከስሞ አንድ ውህድ እና ብልፅግና ፓርቲ የሚባል ተቋቁሟል!!!!
Posted: 21 Nov 2019, 14:49
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ተሰማ፥ ውህደቱን የኢህአዴግ ም/ቤት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ሲገልጡ ካነሷቸው ነገሮች ውስጥ መሠረታዊ የሆነ አንድ ጉዳይ ነበር። ይኸውም ውህደቱን አስመልክቶ የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ አሳልፏቸው ከነበሩ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ውስጥ:- የኢህአዴግ ውህደት በተመለከተ ውህደቱን ለማስፈፀም ለኢህአዴግ ምክርቤት ውክልና ተሰጥቶ ነበር::
እንግዲህ ይህ ማለት ምክርቤቱ በድርጅታዊ ጉባዔው ጉባዔተኞች ውክልና ከተሰጠው፣ በቀጣይ ስለ ውህደት የሚሰበሰብ ድርጅታዊ ጉባዔ አይኖርም ማለት ነው። ስለሆነም ኢህአዴግ በይፋ ዛሬ ከስሞ አንድ ውህድ እና ብልፅግና ፓርቲ የሚባል ተቋቁሟል ማለት ነው። አንዳንድ የኦዴፓ ቋሚ ደጋፊዎች አጀንዳው ገና ለድርጅታዊ ጉባዔ እንደሚቀርብ አድርገው የተረዱና ሲፅፉ የነበሩት ይህንን ውክልና አልሰሙም ነበር ማለት ነው።