
ህወሓት በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቢገኝም ባይገኝም የሚያመጣው ለውጥ የለም!
ህወሓት "በውህደት ሰበብ ህወሓትን የማፍረስ ስልጣን ስለሌለን ህዳር 12/2012 ዓ.ም በሚካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አልገኝም" ብሏል። ይሁን እንጂ ሲጀመር የኢህአዴግን ውህደት ያልተቀበለ አባል ድርጅት በውህደቱ ዙሪያ በሚካሄድ ስብሰባ ላይ መገኘት የለበትም። በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ቢገኝ እንኳን ውህደቱን ለማስቆም የሚያስችል ድምፅ የለውም። በመሆኑም ህወሓት በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቢገኝም ባይገኝም የሚያመጣው ለውጥ የለም::


Re: ህወሓት በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቢገኝም ባይገኝም የሚያመጣው ለውጥ የለም!
"ህወሓትን ለማፍረስ ስልጣን የለንም" የሚሉት ድሮውስ ደደቢት ሲሸፍቱ ማን ስልጣን ሰጣቸው?