ሀገር ከስልጣን በላይ ነው። ከስልጣን ስለተባረርክ ሀገር አፈርሳለሁ ማለት ክሽፈት ነው። ህዝብ ከፓርቲ በላይ ነው፤ ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተጠላች የትግራይ ህዝብን ዕጣ ፈንታ በአንድ ድርጅት ፍላጎት ለመወሰን መፍጨርጨር ያስተዛዝባል። የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም። ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር ይታገላል እንጂ ለህወሓት ዓላማ ሲባል በደሙና በአጥንቱ
የገነባትን ሀገር ጥሎ አይገነጠልም! ትግራዋይነት ኢትዮጵያዊነት ነው!
አብርሃ ደስታ