Page 1 of 1

በአምቦ የአብይ አህመድ ቄሮዎች እና የጃዋር መሀመድ ቄሮዎች ተፋጠው ዲንጋይ እየተወራወሩ ነው!! DW

Posted: 05 Nov 2019, 15:57
by Maxi
በአምቦ የአብይ አህመድ ቄሮዎች እና የጃዋር መሀመድ ቄሮዎች ተፋጠው ዲንጋይ እየተወራወሩ ነው!! DW

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ደጋፊና ተቃዋሚዎች በአምቦ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን በመደገፍ ዛሬ በአምቦ ከተማ ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ተሰረዘ። የድጋፍ ሰልፉ የተሰረዘዉ ሀሳቡን የተቃውሙ ወጣቶች ያሰራጯቸው መልዕክቶች ስጋት በመፈጠራቸዉ ነው ተብሏል።

ሰልፉ ለዛሬ የተጠራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባለፈው ሐሙስ አምቦ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር ሲወያዩ የገጠማቸው ተቃውሞ የከተማዋን ነዋሪ እንደማይወክል ለመግለጽ በሚል እንደሆነ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይን ለመደገፍ ተጠራ የተባለውን ሰልፍ ሲያስተባብሩ ከነበሩ አንዱና «ስሜ አይጠቀስ» ያለ ወጣት እንዳለው የድጋፍ ሰልፍ እንዲደረግ በሚፈልጉና ይህንኑ በሚቃወሙ ወጣቶች መከካከል የከረረ ልዩነት በመፈጠሩ ሰልፉ ቀርቷል።


Audio

https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/ ... wnload.mp3


more
https://www.dw.com/am/የጠቅላይ-ሚንስትር-ዐብይ-ደ ... a-51124917