ከበቡሽ ስለ መከከበብ ያወራል! አንበጣ እንኳን ዓለምአቀፍ ሆኗል! በ1ቀን 87000 ኩንታል ይበላል! ሌላዉ ዓይኑን በጨዉ አጥባል
Posted: 05 Nov 2019, 10:46
በትግራይ እና ወሎ አከባቢ የተከሰተው የአንበጣ ወረርሽኝ በእህል ሰብል እና በእንስሳት መኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ይህ የአንበጣ ወረርሽኝ የመጣው #ከየመን ሲሆን በጅቡቲና ሶማሌላንድ በኩል አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ዘገባው ያስረዳል። ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ሞቃታማ ቦታዎች መራባቱ ተገልጿል። በአከባቢው እየጣለ ያለው ዝናብ ለአንበጣው መራባት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል። በዚህ ምክንያት 174 ስኩዌር ኪሎሜትር (54 ወረዳዎች ወይም 1085 ቀበሌዎች ላይ መራባቱ ተገልጿል። በአንድ ኪሎሜትር ስኩዌር ላይ እስከ 30 ሚሊዮን የሚደርስ አንበጣ ያርፋል። ይህ የአንበጣ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 8700 ሜትሪክ ቶን (87ሺህ ኩንታል) የሚሆን ሰብልና ተክል ቀርጥፎ እየበላ ነው።







