Page 1 of 1

ለመሆኑ የኢትዮጵያው መሪ ኢንተርሃምዌ የተሰኘውን አሸባሪ ድርጅት ያውቁት ይሆን?

Posted: 04 Nov 2019, 13:22
by simbe11
ለመሆኑ የኢትዮጵያው መሪ ኢንተርሃምዌ የተሰኘውን አሸባሪ ድርጅት ያውቁት ይሆን?

በኢትዮጵያ የተከሰተውን አሳዛኝ የዘር ማጥፋት ተከትሎ የተደሶከረውን የጠ/ሚው አስተዛዛቢ መግለጫ ለተከታተለ መቼም ግለሰቡ አገር ለመምራት የሚያስችል አቅም ብቻ ሳይሆን ፍላጎትም እንደሌላቸው ይታዘባል ብዬ እገምታለሁ:: ለቁጥር የታከተ የኢትዮጵያ ልጅ ደሙ ፈሶ ሲያበቃ ሰውየው የስታትስቲክስ ጨዋታ አድርገው ከእከሌ ብሄር ይህን ያህል ከዛኛው ደሞ ይህን ያህል እያሉ አላገጡ::
ጠ/ሚው ድንገት ጆሮ ካሎት በ1993ቱ የርዋንዳ ዘር ፍጅት የተገደሉት አንድ ሚልዮን ቱትሲዎች ብቻ አይደሉም:: አንድ ሚሊዮን ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች እንጂ:: አሁንም ጥቂት አሸባሪዎች የዘር ማጥፋት የፈጸሙት ኢትዮጵያውያን ላይ ነው:: ከዚህ ብሄር ከዛ ብሄር እያሉ ከመምህሮ ትህነግ የተማሩትን ከፋፋይ ዘረኛ ፖለቲካዎን ወዲያ ይበሉ::