Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sholagebya
Member
Posts: 494
Joined: 27 Oct 2014, 15:59

የኃይሌ ገብረሥላሴ “ አህያውን ሲፈሩ ዳውላውን ! “

Post by sholagebya » 03 Nov 2019, 10:43

በቅርቡ በጃዋርና በቄሮዎች የዛምቢ የእንስሳ አይነት ጥቃት የብዙ ወገኖቻችን ህይወት መጥፋት ምክንያት ነው :: ታዲያ ባለፈው ለሃያ-ሰባት አመታት ከወያኔ ጋር ሲሞዳሞድ የነበረው ኃይሌ ገብረሥላሴ “ ፌስቡክን ለመክሰስ እፈልጋለሁ “ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ነው :: ያለፈው የአድርባይነቱ ሚናው እና የትራክ ሪከርዱ ለሕዝብ መብት ለመታገል ምንም አይነት የሞራል ልዕልና የሌለው ሰው አሁን ደርሶ የሕዝብ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት መሞከር የሚያስተዛዝብ
ይሆናል :: እውነት ግን ኃይሌ የአገርና የሕዝብ ተቆርቋሪ ከሆነና በግፍ በቄሮዎችና በጃዋር ጠንሳሽነት ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ከልብ ካዘነ ማውገዝ ያለበት የአብይን መንግስትና ቄሮዎችን ነበር :: ፌስቡክን የግድያው አስፈጻሚ ማድረግና ጥሩ ስሙን ተጠቅሞ “ እከሳለሁ “ ማለት ግን “ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን !” የምንለው አይነት የውሸት ማስፈራሪያ ነው :: ኃይሌ ገብረሥላሴ እኮ “ ዴሞክራሲ ለአፍሪካውያን ቅንጦት ነው !” ያለ ጅል አድርባይ ግለኛ ( selfish ) አይደለምን ???