Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4479
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ህወሓት – ስዩም ተሾመን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደምትገል ማስጠንቀቂያ ላከች

Post by Abaymado » 01 Nov 2019, 10:17

“ሕዝብ ስዩምን ሊጠብቀው ይገባል”

በጃዋር ትዕዛዝ ንጹሃን መጨፍቸፋቸውን፣ መታረዳቸውን፣ የእምነት ተቋማት መቃጠላቸውንና ንብረት መውደሙን ተከትሎ ሴራው እንዴትና በነማን ቅንጅት እንደተቀነባበረ ይፋ በማድረግ ላይ ባለው አምደኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስዩም ተሾመ ላይ የግድያ ዛቻ ተሰነዘረ። የግድያው ዛቻ በቀጥታ የተላከው ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ አባል ጌታቸው ነው።

ህወሓት ፖሊሱን፣ ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ኢኮኖሚውን ከፍተኛውን የአገሪቱን ሥልጣን በተቆጣጠረበት ወቅት በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ጎን ለጎን ትግል ሲያካሂድ የነበረው ስዩም ተሾመ በተደጋጋሚ ታስሯል፣ ቶርቸር ተደርጓል፣ ተሰቃይቷል፣ እንደዜጋ ለምን ጻፍክ በሚል የከፋ ወንጀል ተፈጽሞበታል።

በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ቢያልፍም ግንባሩን ሳያጥፍ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን በብዕሩ ተጋፍጧል። ለውጡ እውን ከሆነ በኋላም ሥራውን አቁሞ “ነጻ ውይይት” በሚል ርዕስ ቃለ መጠይቅ በማቅረብ የህወሓትን ገበና አደባባይ እርቃን አውጥቷል።

ቀድሞም ጥርስ የተነከሰበት ስዩም እሁድ ይፋ እንዳደረገው አቶ ጌታቸው ረዳ ለወሲብ ሲዳራ የሚያሳይ፣ ከጃዋር መሀመድ ጋር አገሪቱን አተራምሶ መንግሥት ለመገለበጥ ያሴሩትን ሤራ የሚያጋልጥ የኢሜል መልዕክቶችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ማስፈራሪያው በቀጥታ የተላከለት።

ዜጎች ጥበቃ ሊያደርጉለት እንደሚገባ በተደጋጋሚ ቢነገርም ስዩም ግን ግንባሩን እንደማያጥፍና እስከወዲያኛው በጀመረው ሥራ እንደሚቀጥል በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።

ህወሓት ከፍተኛ ኃላፊነት የሰጠችውና የፓርላማ አባል የሆነው ጌታቸው የራያን ህዝብ በመሸጡ ብቻ ሳይሆን በሴሰኛነት፣ በዝሙት፣ ሃብት በማሸሽ፣ ከአገር ውጪ ንብረት በማካበት፣ በሶማሊ ክልል የተሞከረው አገር የመበተን አጀንዳ ከከሸፈ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመሩትን መንግሥት በነውጥ ለመጣል ከድብረጽዮን (ጌታቸው አሰፋ) ውክልና ወስዶ በቅማንት፣ በወላይታ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች ለሚፈጸሙ የማተራመስ ዕቅዶች ዋና አስተባባሪ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚህ የጌታቸው ረዳ ዛቻ “ይድረስ ለጌታቸው ረዳ፤ እኔ ያመንኩበትን ሰርቼ እንጂ አንተን ፈርቼ አልሞትም” ስዩም የሰጠው መልስ የሚከተለው ነበር፤

ይህን የኢሜይል መልዕክት የፃፍከው እኔን በማስፈራራት አንተና ድርጅትህ ህወሓት በሀገር ደህንነትና የዜጎች ህይወት ላይ የምትፈፅሙትን ወንጀል ከማጋለጥ እንድታቀብ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እኔን በማስፈራራት ያመንኩበትን ነገር ከማድረግ ለማስቆም መሞከር ሞኝነት ነው። ምክንያቱም ይህን ፈፅሞ ማድረግ አይቻልም። አንድ የማዕከላዊ መርማሪ ልክ አንደ አንተ በእብሪት ተወጥሮ “ጥጋብህ እዚህ ደርሷል! ጠብቅ ቆይ አሳይሃለሁ!” ብሎ ሲዝትብኝ “ሌሊት ላይ ወደ ማሰቃያ ክፍል ወስጄ ጥፍርህን እየነቀልኩ አሰቃይሃለሁ!” ማለቱ እንደሆነ ገምቼያለሁ። ነገር ግን ክፍሌ ውስጥ ገብቼ በፍርሃት ስንበቀበቅ አታገኘኝም። ከዚያ ይልቅ ከእግሬ ጣቶች የአንዱን ጥፍር በገዛ እጄ ነቅዬ ስቃዩን ተለማምጄ ነው የጠበቅኩት!!! አሁን አንተም ይህን ማስፈራሪያ እዚህ ፌስቡክ ላይ ከለጠፍኩት “እንደ ውሻ በድንጋይ ተወግረህና ተሰቃይተህ ትሞታለህ” ብለሃል አይደል?? ቱፍ!! እኔ ወንድ የአባቴ ልጅ ነኝ። ያመንኩበትን ሰርቼ እንጂ ፈርቼ አልሞትም። ይሄው የአንተን ማስፈራሪያ እዚህ አውጥቼ ለጠፍኩት!!! በል እስኪ እንዳልከው ቅጥረኞችህን ላክና ግደለኝ!

ጎልጉል አስተያየት የጠየቃቸው እንደተናገሩት ከሆነ መንግሥት እንደ ጃዋር ላሉት ጥበቃ የሚያቆም ከሆነ በዚያ ተጻራሪ ለአገርና ለሕዝብ ኅልውና በዚህ መልኩ መስዋዕትነት ለሚከፍሉ ዋስትና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

“ስዩም ያለመታከት ከሚወጣቸው መረጃዎች በእጅጉ እየተጠቀመ ያለው ሕዝብ ወገናዊነቱን ለስዩም ጥበቃ በማድረግ ሊወጣ ይገባዋል” ያሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ “አገር ለመበታተንና ሕዝብን ለማጋደል ቀን ተሌት ለሚሠራው ጃዋር ድጋፍ እየሰጡ ካሉት ቄሮዎች የእውነትና የአገር ፍቅር ስሜት ላቸው ትምህርት ቢወስዱ መልካም ነው፤ እነርሱ ለጥፋት ይህንን ያህል ሲተጉ እኛ ደግሞ አገር ለማዳን ለሚሠሩ ከዚህ እጥፍ ልንሠራና ልንተጋ ይገባል” ብለዋል።

በአጠቃላይ አስተያየት የሰጡ እንደተናገሩት ከሆነ ግን እንደዚህ ባለ መልኩ የግድያ ሙከራና ሤራ ከአንድ የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሰነዘር መንግሥት እየሰማ ዝም ማለት የለበትም፤ ጌታቸው ረዳን በኃላፊነት መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ለስዩም ተሾመም ልዩ ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል ብለዋል።


http://www.goolgule.com/tplf-threatens-to-kill-seyoum/

Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: ህወሓት – ስዩም ተሾመን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደምትገል ማስጠንቀቂያ ላከች

Post by Maxi » 01 Nov 2019, 11:31

ስዮም ተሾመ የአብይ አሀመድ ተቀጣሪ አይደለም እንዴ!! ለአሸባሪው ለጃዋር መሃመድ ወታደሮች ቀጥሮ እያስጠበቀው ያለው አብይ አሀም፣እድ ለምን ለስዮም ተሾመስ ወታድሮች ቀጥሮ አያስጠበቀውም።

ቢገሉት የስዮም ተሾመ ህወት በየቀኑ በነ ጃዋር መሀመድ ከሚገደለው ኢትዮጵያዊ ህይወት የበለጠ ነው እንዴ ለእሱ ጠባቂ ወታደሮች የሚቀጠሩለት?

Post Reply