በአሜሪካ የፋይናንስ ህግ መሰረት በዚህ መልኩ የገንዘብ ዝውውር መፈፀም ብዙ አመት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። ባለፉት ሁለት ወራት ይህን ሀገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሰማራውን ድርጅት ስምና አድራሻ ለማወቅ ጥረት አድርጌ አልተሳካልኝም ነበር። ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የኢሜይል አድራሻ አፈትልኮ በወጣው መረጃ መሰረት የተተቀሰውን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚያከናውነው ድርጅት ተስፋዛጊ አበራ እና አቶ አሉላ ሰለሞን፣ እንዲሁም በዶ/ር ደብረፂዮን ዕውቅና የተቋቋመ መሆኑ ተደርሶበታል። ከታች በቀረበው የኢሜይል ማስረጃ መሰረት ባለፈው አመት መጨረሻ አከባቢ አቶ አሉላ ሰለሞን እና ተስፋይዘጊ መቀሌ በሚገኘው ፕላኔት ሆቴል ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሰማራ ድርጅት ለማቋቋም መስማማታቸው ተገልጿል። ለአቶ አሉላ ሰለሞን በተፃፈው የኢሜይል መልዕክት መሰረት ድርጅቱ ህወሓት እና የኢፈርት ድርጅቶች ያጋጠማቸውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል። ድርጅቱም ከ20 በላይ አባላት እንደሚኖሩት ሲሆን በዋናነት ለትግራይ ቀና አመለካከት ያላቸው ወይም የህወሓት አባላት/ደጋፊ መሆን እንዳለባቸው ተጠቅሷል። ድርጅቱን በማቋቋም ረገድ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አፈትልኮ በወጣው የኢሜይል መልዕክት ውስጥ ተገልጿል። ቀጣይ ስራዎችን ደግሞ በአቶ አሉላ ሰለሞን በኩል እንዲከናወኑ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የዚህን ህገወጥ ድርጅት መቋቋም አስመልክቶ በአቶ ተስፋይገዚ በኩል እንዲያውቁት መደረጉን ከታች ከለው የኢሜይል መረዳት ይቻላል። በአጠቃላይ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፂዮን ዕውቅና የተቋቋመው ድርጅት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ስራ የተሰማራ ሲሆን በአሜሪካን ዋሽንግተን የሚገኘው አቶ አሉላ ሰለሞን ደግሞ ይህን ህገወጥ ተግባር በበላይነት እያስተባበረ ይገኛል። አቶ አሉላ ሰለሞን ቀንደኛ የህወሓት ደጋፊ ሲሆን ከአመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት አሜሪካ ውስጥ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። ህወሓትን በመወከል በአሜሪካ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግ ይታወቃል። ከዶ/ር ደብረፂዮን ኢሜይል አፈትለኮ በወጣው መረጃ መሰረት ደግሞ አቶ አሉላ ሰለሞን በአሜሪካ የተቋቋመውን ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ድርጅት መስራችና መሪ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
EthioWikiLeaks

