ዶ/ር ገባዎ ቲቤሶ (Gebawo Tibesso) የአርሲ ዩኒቨርስቲ መምህር፤ ዛሬ ጠ/ሚ አብይና ኦቦ ለማ የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወካዮችን አወያይተው በነበረበት መድረክ የነበረውን ጥያቄና መልስ በአፋን ኦሮሞ ለተከታዮቻቸው አጋርተዋል፡፡
[ቋንቋውን በአግባቡ የሚችል ወዳጃችን ወደ አማርኛ ተርጉሞልናል፡፡]
ከታዳሚው ህዝብ የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየት አንከኳር ነጥቦች፡-
……
1. ህዝብ አደባባይ የወጣው ጅዋርን ለመደገፍ እንጂ ረብሻ ለማንሳት አይደለ
2. የተፈጠረውን ችግር አውጥታችሁ ለህዝብ ካልገለጻችሁ፤ ብዙ ከዚህ የባሰ ችግር ይፈጠራል
3. አብይና ለማ በትክክል ኦሮሞ ከሆናችሁ ይህን ችግር ፍቱ
4. ለህዝባችን ደህንነት የሚሰጠው ጥበቃ ለምን የላላ ሆነ
5. የኦሮሞን ህዝብ በተለየ አይን ለምን አታዩም
6. ለሚፈጠሩ ችግሮች ለምን ፈጣን መልስ በመስጠት አታረጋጉም
7. መንግስት ቁጭ ብሎ እራሱን ማየት መመርመር አለበት
8. ያ ማታ በለሊት የጅዋር ቤት የሄደው ሰውዬ የእናንተ ነው ወይስ አይደለም
9. ለማ ሆይ፤ ጠገብንህ ወይስ ጠገብከን (ብዙ ግልጽ አልሆነችልኝም)
10. ኦ ኤም ኤን ያኔ በህወሃት ዘመን፤ ቆርቆሮ ላይ እየወጡ ዲሽ ሲነቅሉም አልተዘጋም
11. በኦሮሞ ልብና አይምሮ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውን ሰው ባትነካኩ ጥሩ ነው…. እና የመሳሰሉ ብዙ ጥያቄዎእች የተነሱ ሲሆን፤ ጠ/ሚ አቢይ እና ለማ መገርሳየሚከተለውን አንኳር መልሶች መልሰዋል፡፡
ለማ መገርሳ የሰጡት መልስ
……………..
1. ጅዋር ላይ የደረሰው ችግር በማንኛውም አቅጣጫ ቢታይ ትክክል አይደለም፡፡ ጉዳዩን መርምረን ወደ ህግ የምንወስደው ይሆናል
2. እኛ የማንወያይ ከሆነ በጠራራ ጸሃይ ውሻ ይበላናል
3. እኔና አብይ እዚህ ወንበር ላይ የተቀመጥነው በኦሮሞ ወጣቶች ደምና አጥንት መስዋእትነት ነው፡፡ እኛ ይህን ከዘነጋን ፈዛዛ/ጅል ሆነናል ማለት ነው
4. እኛ ብንኖርም ባንኖርም የኦሮሞ ትግል ወደ ኋላ የሚመለስ አይደለም
…
የጠ/ሚ አቢይ መልስ
………………..
1. እኛ ተዋርደን እናንተንም ማዋረድ አንፈልግም
2. የኦሮሞን ጥያቄ በሳይንሳዊ መንገድ እየሰራን ነው እንጂ ዝም አላልንም
3. እኔና ለማ አንድ ላይ የተመለስነው ለኦሮሞ ለመስራት ነው እንጂ ኦሮሚያን ለመጉዳት አይደለም
4. ኦሮሚያን ለማስተዳደር ኦሮሚያን ማስተዳደር መሃል ልዩነት የለም (ምን ማለት ተፈልጉ ነው… ግልጽ አይደለችም)
5. እኛ ጅዋርን መግደል ወይም ማሰር ብንፈልግ ሮ ለምን ጥበቃ መደብንለት….
6. እንኳን ጅዋር ይቅርና ማንም እንዲነካ አንፈልግም
7. እኔ ባጠፋ ኑ እና አባሩኝ
8. እኛ ሰራነው ታሪክ ውሎ አድሮ እራሱ የማይናገር ከሆነ፤ መጀመሪያውኑ ታሪክ አልሰራንም ማለት ነው፡፡
Please wait, video is loading...