Page 1 of 1

ህወሀት/ወያኔ በሁሉም አቅጣጫ እንደአጎዛ ቆዳ የተወጠረችበት ሁኔታ ነው ያለው!! ---ለክቡር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ

Posted: 22 Oct 2019, 20:31
by MatiT
ህወሀት/ወያኔ በሁሉም አቅጣጫ እንደአጎዛ ቆዳ የተወጠረችበት ሁኔታ ነው ያለው!! ---
<< የኤርትራው ፕሬዝደንት ለህወሀት መግለጫ ምላሸ ሰጡ! >>
** የባህታዊ ቀበሮ መግለጫና ሽምግልና ለኤርትራ ህዝብ ሰሚ እና ተቀባይነት የሌለው የገደል ላይ ጩኸት ነው!!
ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ፕሬዝዳንት
የትህነግ መራሹ መንግስት የተለመደውን ከስብሰባ ማዕግስት የሚያውጣውን የአስመሳይነት መግለጫ ያደገበት የመሰሪነት ባህሪው ነው ሲሉ ገለፁ።
** ባለፉት ሃያ ዓመታት በዚህ የመሰሪነት ተፈጥሮው የአንድ እናት ልጆችን በማለያየት የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ህዝብ በመግለጫ በመሽንገል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መንግስታዊ የጥፋት ሥራ ሲሰራ መቆየቱ አለም የሚያውቀው የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
** በህዝብ ትግል ሀጢያት ከሚሰራበት በትረ ስልጣን የተወገድ ቢሆን ሀገሪቱ ሰላማዊ ሆና ያላትን ተፈጥሮዊ ፀጋ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንዳትተርፍ በተልዕኮ የተለመደውን የማተራመስ እና ከእኔ በላይ ለአሳር ነው የሚል ግትርነት ከአንድ ዓመት በመያዝ ሲደመር እና ሲቀነስ እንደቆየ ለኤርትራ ህዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡
** እውነታው ይህ ሆኖ እያለ በተደጋጋሚ ከስብሰባ ማዕግስት በተለመደው የመሰሪነት ባህሪ የሚሰጥ መግለጫ ለኤርትራ ህዝብ ሰሚ እና ተቀባይነት የሌለው የገደል ላይ ጩኸት ነው፡፡
** "ድመት መልኩሳ አመሏን አትረሳ" አለ አማራ እውነቱን እኮ ነው፡፡ መቼም ቢሆን በተለያዩ ሀገሮች አምባሳደራት እና የሀገር መሪዎች የሚደረግ መርህ አልባ ሽምግልና የፓርቲ መግለጫ የባህታዊ ቀበሮ ባህሪ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ለኤርትራ ህዝብ ውሃ የማይቋጥር ተግባር እና ሀሳብ ነው፡፡ ምክንያቱም
1ኛ/ የእኛ በመርህ ላይ የተመሰረተው ግንኙነታችን ከክልል መንግስት ጋር ሳይሆን ከፌድራል መንግስት ጋር ነው፡፡
2ኛ/ ምንም እንኳን የትግራይ ህዝብ ከህዝባችን ጋር የቋንቋና የባህል ተመሳሳይነት ቢኖርውም መሪ ድርጅቱ ትህነግ አብሮት ለታገለው ለአማራ ህዝብ ያልሆነ ለኤርትራ ህዝብ ይበጃል ብለን አናምነም፡፡
3ኛ/ባለፈው ሃያ ዓመት በትህነግ መሰሪነት የኤርትራ ህዝብ ከሁለተኛ ሀገሩ በመሰሪው ትህነግ ተንኮል ሀብት ንብረታችውን ጥለው ሲፈናቀሉ፤ ባለማተቡ የአማራ ህዝብ “ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ" በማለት የህዝባችን ንብረት እና ሀብት መልሷል፡፡ በመሆኑም ትህነግ የአማራን ህዝብ ጠላት በማድረግ በደል ያደረሰበት በመሆኑ ይቅርታ ሳይጠይቅ ከአማራ ጠላት ጋር ህብረት አንመሰረትም፡፡
4ኛ/ ትህነግ ከእኔ በላይ ላሳር በሚል የማያረጅ ግትርነት ባህሪው ጋር ያለፍቺ የተጋባ በመሆኑ ለጋራ ተጠቃሚነት እና እኩልነት አለርጂ ነው፡፡
ሰለሆነም ለጊዜያው ትዳር ብለን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የጀመረነው አዲስ ህብረት በምንም ታምር አናደናቅፍም፡፡
** የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኤርትራ ህዝብ አብሮነት በቀበሮ ባህታዊ መግለጫ እና መርህ አልባ የሽምግልና ጋጋታ አይደናቀፍም!!
ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈውሪቄ የኤርትራ ፕሬዝዳንት
04/02/2012 ዓ.ም - አስመራ
=> ማስታወሻ፦ ፅሁፉ ከኤርትራውያን ወንድሞቻችን ፔጅ ላይ ተወስዶ ወደአማርኛ የተተረጎመ ነው።
እንወድሃለን ወዲአፎም!!

Re: ህወሀት/ወያኔ በሁሉም አቅጣጫ እንደአጎዛ ቆዳ የተወጠረችበት ሁኔታ ነው ያለው!! ---ለክቡር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ

Posted: 22 Oct 2019, 22:35
by Digital Weyane
Down Down Issayas!
Viva Digital Weyane!